ዘሌዋውያን 19:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)36 ትክክለኛም ሚዛን፥ ትክክለኛም መመዘኛ፥ ትክክለኛም የኢፍ መስፈሪያ፥ ትክክለኛም የኢን መስፈሪያ ይኑሩአችሁ፤ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም36 የጽድቅ መለኪያ፣ የጽድቅ ሚዛን፣ የጽድቅ የኢፍ መስፈሪያ፣ የጽድቅ የሂን መስፈሪያም ይኑራችሁ። ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም36 ትክክለኞች የሆኑ ሚዛኖች ማለት የርዝመት፥ የክብደትና የፈሳሽ መለኪያዎች ይኑሩአችሁ፤ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)36 የእውነትም ሚዛን፥ የእውነትም መመዘኛ፥ የእውነትም የፈሳሽ መስፈሪያ ይሁንላችሁ፤ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እኔ ነኝ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)36 የእውነትም ሚዛን፥ የእውነትም መመዘኛ፥ የእውነትም የኢፍ መስፈሪያ፥ የእውነትም የኢን መስፈሪያ ይሁንላችሁ፤ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እኔ ነኝ። ምዕራፉን ተመልከት |