Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 19:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 “ማናቸውም ሰው በባርነት ሥር ካለች ሴት ጋር ቢተኛ፥ እርሷም ለሌላ ሰው ታጭታ ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ ያልተዋጀች ወይም አርነት ያልወጣች ብትሆን፥ ይህ አድራጎት ቅጣት ይረኖረዋል፤ ሆኖም አርነት አልወጣችምና አይገደሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 “ ‘አንድ ሰው ለሌላ ከታጨች ሴት ባሪያ ጋራ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ ሴቲቱም ያልተዋጀች ወይም ነጻ ያልወጣች ብትሆን ይቀጣል፤ ነገር ግን ሴቲቱ ነጻ ስላልወጣች አይገደሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 “አንድ ሰው ልጃገረድ የሆነች አገልጋዩን ለሌላ ሰው ቊባት ትሆን ዘንድ ለመሸጥ ካስማማ በኋላ ገዢው ገንዘቡን ከፍሎ ከመጨረሱ በፊት ሻጩ ከልጃገረዲቱ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት ቢያደርግ ሁለቱም ይቀጣሉ፤ ሆኖም እርስዋ ገና ነጻ ያልወጣች አገልጋዩ ስለ ሆነች የሞት ቅጣት አይፈጸምባቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 “ማና​ቸ​ውም ሰው ከሴት ባሪያ ጋር ቢተኛ፥ እር​ስ​ዋም ለባል የተ​ሰ​ጠች፥ ዋጋ​ዋም ያል​ተ​ከ​ፈለ፥ አር​ነት ያል​ወ​ጣች ብት​ሆን፥ ቅጣት አለ​ባ​ቸው፤ አር​ነት አል​ወ​ጣ​ች​ምና አይ​ገ​ደ​ሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ማናቸውም ሰው ከሴት ባሪያ ጋር ቢተኛ፥ እርስዋም ለባል የተሰጠች ዋጋዋም ያልተከፈለ አርነት ያልወጣች ብትሆን፥ ቅጣት አለባቸው፤ አርነት አልወጣችምና አይገደሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 19:20
3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብርሃም አንዱን ከባርያይቱ ሌላኛውንም ከነጻይቱ የሆኑ ሁለት ልጆች እንደነበሩት ተጽፎአል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች