Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 19:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲህ ብለህ ተናገር፦ እኔ ጌታ አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “ለመላው የእስራኤል ሕዝብ ጉባኤ እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፤ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “ለእስራኤል ሕዝብ ይህን ንገር፦ ‘እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ እን​ዲህ በላ​ቸው፦ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ቅዱስ ነኝና እና​ንተ ቅዱ​ሳን ሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲህ ባላቸው፦ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 19:2
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቅዱስ ነውና ሁሉም ታላቅና ግሩም ስምህን ያመስግኑ።


የካህናት መንግስት፥ የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ። ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው።”


ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


እኔ ጌታ ቅዱስ ነኝና፥ ለእኔም እንድትሆኑ ከአሕዛብ ለይቻችኋለሁና እናንተ ለእኔ ቅዱሳን ሁኑ።


እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝና፤ ስለዚህ ራሳችሁን ቀድሱ፥ ቅዱሳንም ሁኑ።


ስለዚህ በሕዝቡ መካከል ዘሩን አያርክስ፤ እኔ የምቀድሰው ጌታ ነኝና።”


ነገር ግን ነውረኛ ነውና መቅደሶቼን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይግባ፥ ወደ መሠዊያውም አይቅረብ፤ የምቀድሳቸው እኔ ጌታ ነኝና።”


የአምላክህን እንጀራ ያቀርባልና ስለዚህ ትቀድሰዋለህ፤ እኔም የምቀድሳችሁ ጌታ ቅዱስ ነኝና እርሱ ቅዱስ ይሆንልሃል።


“በውኑ ሁለት ሰዎች ተቀጣጥረው ሳይገናኙ በአንድነት ሊሄዱ ይችላሉን?


ስለዚህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ።


እንግዲህ ወዳጆች ሆይ! ይህ ተስፋ ቃል ስላለን፥ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ፥ እግዚአብሔርን በመፍራት ቅድስናችንን ፍጹም እናድርግ።


ዓለም ሳይፈጠር፥ በፍቅር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን እድንሆን በክርስቶስ መረጠን።


ጌታ እግዚአብሔርን ታዘዝ፤ ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ጠብቅ።”


ኢያሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “እርሱ ቅዱስ አምላክ ነውና፥ እርሱም ቀናተኛ አምላክ ነውና ጌታን ማገልገል አትችሉም፤ መተላለፋችሁንና ኃጢአታችሁን ይቅር አይልም።


እንደ ጌታ ያለ ቅዱስ የለም፥ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤ አምላካችንን የሚመስልም ዓለት የለም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች