Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 18:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 በእርግጥ ማንም ሰው ርኩሰት ከሆኑት ከእነዚህ ነገሮች ማናቸውንም ነገር ቢያደርግ፥ ያደረጋችው ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 “ ‘ከእነዚህ አስጸያፊ ድርጊቶች ማንኛውንም የሚፈጽም ሰው ሁሉ ከወገኑ ተለይቶ ይጥፋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እነዚህን ርኲሰቶች የሚፈጽም ያ ሰው ከሕዝቡ ይለይ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ከዚህ ርኵ​ሰት ሁሉ ማና​ቸ​ውን የሚ​ያ​ደ​ርግ ያ ሰው ከሕ​ዝቡ መካ​ከል ተለ​ይቶ ይጠ​ፋ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ከዚህ ርኵሰት ሁሉ ማናቸውን የሚያደርግ ያ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 18:29
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያው ቀን ከቤቶቻችሁ እርሾ ታስወግዳላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን የቦካ የሚበላ ያቺ ነፍስ ከእስራኤል ተለይታ ትጥፋ።


እንደ እርሱ ዓይነት የሚቀምም ሰው ወይም ከእርሱ በሌላው ላይ የሚያፈስስ ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።’”


“ከእስራኤልም ልጆች ወይም በመካከላቸው ከሚኖር እንግዳ ማናቸውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቊርበታለሁ፥ ያንንም ሰው ከሕዝቡ መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።


ያለዚያ ግን ምድሪቱን ካረከሳችሁ እርሷ ከእናንተ በፊት የነበረውን ሕዝብ አንቅራ እንደ ተፋች እንዲሁ እናንተንም አንቅራ ትተፋችኋለች።


ስለዚህ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ ላይ የተደረገውን ጸያፍ ወግ ሁሉ ፈጽሞ እንዳታደርጉ፥ በእርሱም ራሳችሁን ፈጽሞ እንዳትረክሱ ሥርዓቴን ጠብቁ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።”


“የሙታን መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም በሚከተል፥ በሥራቸውም በሚያመነዝር፥ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቊራለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።


ነገር ግን የረከሰ ሰው ሆኖ ሳለ፥ ለጌታ ከሆነው ከአንድነት መሥዋዕት ሥጋ የበላ እንደሆነ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።


ማንም ሰው የሰውን ርኩሰት ወይም የረከሰን እንስሳ ወይም ምንም ዓይነት ርኩስ ሆኖ የተጠላን ማናቸውንም ርኩስ ነገር ነክቶ፥ ለጌታ ከሆነው ከአንድነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።”


ይህን ከሚያደርግ ሰው፥ የሚጠራውንና የሚመልሰውን ለሠራዊትም ጌታ ቁርባን የሚያቀርበውን ከያዕቆብ ድንኳን ያጠፋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች