ዘሌዋውያን 18:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 በእርሱም ራስህን እንዳታረክስ ከማናቸውም እንሰሳ ጋር አትተኛ፤ ሴት ከእርሱ ጋር ለመተኛት በእንስሳ ፊት አትቁም፤ ጸያፍ የሆነ ተግባር ነው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 “ ‘ከእንስሳ ጋራ ግብረ ሥጋ በመፈጸም ራስህን አታርክስ። ሴትም ከእንስሳ ጋራ ግብረ ሥጋ ለመፈጸም ራሷን አታቅርብ፤ ይህ አስጸያፊ ምግባር ነው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ወንድ ወይም ሴት ማንም ሰው ከእንስሳ ጋር ተኝቶ ራሱን አያርክስ፤ እንዲህ ያለው ድርጊት የተፈጥሮን ሕግና ሥርዓት የሚያበላሽ ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ዘርህን በእርስዋ ላይ እንዳትዘራና እንዳትረክስባት ወደ እንስሳ አትሂድ፤ ሴት ከእርሱ ጋር ትተኛ ዘንድ በእንስሳ ፊት አትቁም፤ የተጠላ ነገር ነውና። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 እንዳትረክስባትም ከእንሰሳ ጋር አትተኛ፤ ሴት ከእርሱ ጋር ትተኛ ዘንድ በእንስሳ ፊት አትቁም፤ የተጠላ ነገር ነውና። ምዕራፉን ተመልከት |