ዘሌዋውያን 17:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ስለዚህ ተከትለዋቸው ላመነዘሩባቸው ለሰይጣናት ከእንግዲህ ወዲህ መሥዋዕታቸውን አይሠዉም። ይህ ለእነርሱ ለልጅ ልጃቸው ለዘለዓለም ሥርዓት ይሁን። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ከዚህ በፊት ላመነዘሩባቸው አጋንንት ከእንግዲህ ወዲህ ማንኛውንም መሥዋዕት ሊሠዉ አይገባም። ይህ ለእነርሱና ከእነርሱ በኋላ ለሚነሣው ትውልድ ሁሉ የዘላለም ሥርዐት ይሁን።’ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 የእስራኤል ሕዝብ ከእምነታቸው ለሚያርቁአቸው አጋንንት መሥዋዕት አድርገው እንስሶቻቸውን በየሜዳው በማረድ በእግዚአብሔር ላይ ማመፅ አይገባቸውም፤ እስራኤላውያን ይህን ሥርዓት በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ይጠብቁት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 መሥዋዕታቸውንም ደግሞ ተከትለው ላመነዘሩባቸው ለሰይጣናት አይሠዉ። ይህ ለእነርሱ ለልጅ ልጃቸው ለዘለዓለም ሥርዐት ይሁን።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 መሥዋዕታቸውንም ደግሞ ተከትለው ላመነዘሩባቸው ለሰይጣናት አይሠዉ። ይህ ለእነርሱ ለልጅ ልጃቸው ለዘላለም ሥርዓት ይሁን። ምዕራፉን ተመልከት |