ዘሌዋውያን 16:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ከዚያም በኋላ በጌታ ፊት ወዳለው ወደ መሠዊያው ይወጣል፤ ለእርሱም ያስተሰርይለታል፤ ከወይፈኑም ደም ከፍየሉም ደም ወስዶ በመሠዊያው ዙሪያ ያሉትን ቀንዶች ያስነካል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 “ከዚያም መጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ወዳለው መሠዊያ ይምጣ፤ ለመሠዊያውም ያስተስርይለት፤ ከወይፈኑና ከፍየሉ ደም ወስዶ የመሠዊያውን ቀንዶች ሁሉ ያስነካ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ከዚያም በእግዚአብሔር ፊት ወዳለው መሠዊያ ወጥቶ መሠዊያውን ያንጻው፤ ከኰርማውና ከፍየሉ ጥቂት ደም ወስዶ በመሠዊያው ዙሪያ ያሉትን ጒጦች ይቀባ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 በእግዚአብሔርም ፊት ወዳለው ወደ መሠዊያው ወጥቶ ያስተሰርይለታል፤ ከወይፈኑም ደም፥ ከፍየሉም ደም ወስዶ በመሠዊያው ዙሪያ ያሉትን ቀንዶች ያስነካል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 በእግዚአብሔርም ፊት ወዳለው ወደ መሠዊያ ወጥቶ ያስተሰርይለታል፤ ከወይፈኑም ደም ከፍየሉም ደም ወስዶ በመሠዊያው ዙሪያ ያሉትን ቀንዶች ያስነካል። ምዕራፉን ተመልከት |