Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 15:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 “አንዲትም ሴት ከወር አበባዋ ቀን ሌላ ደምዋ ብዙ ቀን ቢፈስስ፥ ወይም ደምዋ ከወር አበባዋ ጊዜያት የሚበልጥ ቢፈስስ፥ ፈሳሹ ነገር በሚፈስስበት ቀን ሁሉ በርኩስነትዋ ትቀጥላለች፤ በወር አበባዋ ጊዜያት እንደ ሆነች እንዲሁ እርሷ ርኩስ ትሆናለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “ ‘ሴት ከወር አበባዋ ጊዜ ሌላ ብዙ ቀን ደም ቢፈስሳት፣ ወይም የወር አበባዋ ጊዜ ካለፈ በኋላ የደሙ መፍሰስ ባይቋረጥ፣ ልክ እንደ ወር አበባዋ ጊዜ፣ ደም መፍሰሱ እስኪቆም ድረስ ርኩስ ትሆናለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “አንዲት ሴት ከወር አበባዋ ወቅት አልፎ ለብዙ ቀን የሚፈስ ወይም ከተመደበው የወር አበባዋ በኋላ ባለማቋረጥ የሚፈስ ደም ቢኖራት፥ ደሙ እስከሚቆምበት ጊዜ ድረስ ልክ በወር አበባዋ ጊዜ እንደ ነበረችበት ሁኔታ የረከሰች ትሆናለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 “ሴትም ከግ​ዳ​ጅዋ ቀን ሌላ ደምዋ ብዙ ቀን ቢፈ​ስስ፥ ወይም ደምዋ ከግ​ዳ​ጅዋ ወራት በኋላ ቢፈ​ስስ፥ በግ​ዳ​ጅዋ ወራት እንደ ሆነች እን​ዲሁ በፈ​ሳ​ሽዋ ርኩ​ስ​ነት ወራት ትሆ​ና​ለች፤ ርኵ​ስት ናት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ሴትም ከመርገም ቀን ሌላ ደምዋ ብዙ ቀን ቢፈስስ፥ ወይም ደምዋ ከመርገምዋ ወራት የሚበልጥ ቢፈስስ፥ በመርገምዋ ወራት እንደ ሆነች እንዲሁ በፈሳሽዋ ርኵስነት ወራት ትሆናለች፤ ርኩስ ናት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 15:25
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፈሳሹም ነገር በሚፈስስበት ጊዜያት ሁሉ የምትተኛበት መኝታ ሁሉ በወር አበባዋ ጊዜ እንደነበረው መኝታ ያለ ይሆንባታል፤ የምትቀመጥበትም ነገር ሁሉ እንደ ወር አበባዋ ርኩስነት ርኩስ ይሆናል።


እነሆ ለዐሥራ ሁለት ዓመታት ደም የሚፈስሳት ሴት ከኋላው ተጠግታ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤


ለዐሥራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈስሳት የኖረችም ሴት በዚያ ነበረች፤


ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፤ ያላትንም ንብረት ሁሉ ተጠቅማ ለባለመድኃኒቶች ብታውልም ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች