ዘሌዋውያን 15:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ማንም ሰው ከእርሷ ጋር ተኝቶ የወር አበባዋ ቢነካው፥ እርሱ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል፤ የሚተኛበትም መኝታ ሁሉ ርኩስ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 “ ‘አንድ ሰው ከርሷ ጋራ ቢተኛና የወር አበባዋ ቢነካው፣ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እርሱ የሚተኛበት መኝታ ሁሉ ርኩስ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 በወር አበባዋ ወቅት ከእርስዋ ጋር የሚተኛ ወንድ ቢኖር እርሱም እንደ እርስዋ የረከሰ ይሆናል፤ ስለዚህም እስከ ሰባት ቀን ድረስ ርኩስ ሆኖ ይቈያል፤ እርሱ የሚተኛበትም አልጋ ርኩስ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ማንም ከእርስዋ ጋር ቢተኛ፥ ግዳጅዋም ቢነካው፥ ሰባት ቀን ርኩስ ነው፤ የሚተኛበትም መኝታ ሁሉ ርኩስ ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ማንም ከእርስዋ ጋር ቢተኛ መርገምዋ ቢነካው፥ ሰባት ቀን ርኩስ ነው፤ የሚተኛበትም መኝታ ሁሉ ርኩስ ነው። ምዕራፉን ተመልከት |