Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 15:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው ከፈሳሹ ነገር ሲነጻ፥ ስለ መንጻቱ ሰባት ቀን ይቈጥራል፤ ልብሱንም ያጥባል፥ ገላውንም በምንጭ ውኃ ይታጠባል፥ እርሱም ንጹሕ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው ከፈሳሹ ሲነጻ፣ በሕጉ መሠረት ለመንጻቱ ሰባት ቀን ይቍጠር፤ ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በምንጭ ውሃ ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “ፈሳሽ ያለበት ሰው ከፈሳሽ በሽታው በዳነ ጊዜ የነጻ እንዲሆን እስከ ሰባት ቀን ድረስ ይቈይ፤ ከዚያም በኋላ ልብሱን ይጠብ፤ በንጹሕ የምንጭ ውሃም ገላውን ይታጠብ፤ የነጻም ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 “ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ሰው ከፈ​ሳሹ ነገር ሲነጻ ስለ መን​ጻቱ ሰባት ቀን ይቈ​ጥ​ራል፤ ልብ​ሶ​ቹ​ንም ያጥ​ባል፤ ገላ​ው​ንም በም​ንጭ ውኃ ይታ​ጠ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው ከፈሳሹ ነገር ሲነጻ ስለ መንጻቱ ሰባት ቀን ይቈጥራል፤ ልብሱንም ያጥባል፥ ገላውንም በምንጭ ውኃ ይታጠባል፥ ንጹሕም ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 15:13
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የነጻውም ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ጠጉሩንም ሁሉ ይላጫል፥ በውኃም ይታጠባል፥ ንጹሕም ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገባል፥ ነገር ግን ከድንኳኑ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀመጣል።


እናንተን በቅድስና ማዕረግ ለመሾም ሰባት ቀን ይወስዳልና የክህነታችሁ ቀን እስኪፈጸም ድረስ ሰባት ቀን ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትውጡ።


ከፈሳሽዋም ብትነጻ ሰባት ቀን ትቈጥራለች፥ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ትሆናለች።


መኝታውንም የሚነካ ማንም ሰው ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።


እንዲሁም ከታመነው ምስክር፥ ከሙታን በኩር ከሆነው፥ የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ፤ ለወደደን፥ ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥


ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች! እጃችሁን አንጹ፤ እናንተ በሁለት ሐሳብ የምትዋልሉ ልባችሁን አጥሩ።


እንግዲህ ወዳጆች ሆይ! ይህ ተስፋ ቃል ስላለን፥ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ፥ እግዚአብሔርን በመፍራት ቅድስናችንን ፍጹም እናድርግ።


በእኔም ላይ ከሠሩት ከበደላቸው ኃጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ፤ በእኔም ላይ ያመፁትንና የሠሩትን የበደላቸውን ኃጢአት ሁሉ ይቅር እላለሁ።


ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አባትዋ ምራቁን በፊትዋ ቢተፋባት እንኳ እርሷ ሰባት ቀን ልታፍር አይገባትምን? ሰባት ቀን ከሰፈሩ ውጪ ተዘግቶባት ትቀመጥ፥ ከዚያም በኋላ ትመለስ።”


“በስምንተኛውም ቀን ነውር የሌለባቸውን ሁለት ተባት ጠቦት፥ ነውር የሌለባትንም አንዲት የዓመት እንስት ጠቦት፥ ለእህሉም ቁርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ዘይትም ያለበትን አንድ የሎግ መስፈሪያ ይወስዳል።


በስምንተኛውም ቀን እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ አሮንንና ልጆቹን የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ጠራ።


ሰባት ቀን ለመሠዊያው ማስተስረያ ታደርጋለህ፥ ትቀድሰዋለህም፤ መሠዊያውም ፍጹም ቅዱስ ይሆናል፤ መሠዊያውን የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።


ለአሮንና ለልጆቹ እነዚህ ያዘዝሁህን ሁሉ አድርግ፤ ሰባት ቀን እጆቻቸውን ትቀድሳለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች