Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 14:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ካህኑ ደዌ ያለባቸውን ድንጋዮች እንዲያወጡ፥ ከከተማውም ውጭ ወደ ረከሰው ስፍራ እንዲጥሉአቸው ያዝዛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ካህኑ የተበከሉት ድንጋዮች ተሰርስረው እንዲወጡና ከከተማው ውጭ ባለው ርኩስ ስፍራ እንዲጣሉ ይዘዝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 የሻጋታው ምልክት ያለባቸው ድንጋዮች ተፈልፍለው ወጥተው ከከተማው ውጪ በሚገኘው በረከሰ ጒድፍ ማከማቻ እንዲጣሉ ይዘዝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 እነ​ሆም፥ ደዌው በቤቱ ግንብ ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ ደዌ ያለ​ባ​ቸ​ውን ድን​ጋ​ዮች እን​ዲ​ያ​ወጡ፥ ከከ​ተ​ማ​ውም ወደ ውጭ ወደ ረከ​ሰው ስፍራ እን​ዲ​ጥ​ሉ​አ​ቸው ያዝ​ዛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ካህኑ ደዌ ያለባቸውን ድንጋዮች እንዲያወጡ፥ ከከተማውም ወደ ውጭ ወደ ረከሰው ስፍራ እንዲጥሉአቸው ያዝዛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 14:40
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ውሻዎችና አስማተኞች፥ ሴሰኛዎችም፥ ነፍሰ ገዳዮችም፥ ጣዖት አምላኪዎችም፥ ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ ይቀራሉ።


ዳሩ ግን ‘ነቢይ ነኝ’ የምትለውን፥ ባርያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ችላ ስለምትላት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤


ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔም የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ትጠላለህ።


“ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንደማትችል፥ እንዲሁም ሐዋርያት ሳይሆኑ ‘ነን’ የሚሉትን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤


መለያየትን የሚያሥነሣ ሰው አንዴና ሁለቴ ከገሠጽኸው በኋላ እንዲህ ከሚመስል ሰው ራቅ።


በውጭ ባሉት ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት።


በእኔ ያለውን ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል።


እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ቤተ ክርስቲያንንም ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ቁጠረው።


ፌዘኛን ብታስወጣ ክርክር ይቆማል፥ ጠብና ስድብም ያልቃል።


ባልንጀራውን በቀስታ የሚያማን እርሱን አሳደድሁ፥ በዓይኑ ትዕቢተኛ፥ በልቡ ኩራተኛ የሆነውን አልታገሥም።


ካህኑም በሰባተኛው ቀን ተመልሶ ያያል፤ እነሆም፥ ደዌው በቤቱ ግድግዳ ላይ ቢሰፋ፥


የቤቱንም ውስጥ ዙሪያውን ያስፍቀዋል፤ የፋቁትንም የምርጊቱን አፈር ከከተማው ውጭ ወደ ረከሰ ስፍራ ያፈስሱታል።


ልብሱንም ያወልቃል፥ ሌላም ልብስ ይለብሳል፤ አመዱንም ተሸክሞ ከሰፈሩ ውጭ ወደ ሆነ ወደ ንጹሕ ስፍራ ያወጣዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች