Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 14:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 “ለመንጻቱ የሚቀርበውን ነገር መግዛት አቅሙ ለማይፈቅድለት የለምጽ ደዌ ላለበት ሰው ሕጉ ይህ ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ተላላፊ የቈዳ በሽታ ይዞት የሚነጻበትን መደበኛ መሥዋዕት ለማቅረብ ዐቅም ላነሰው ሰው ሕጉ ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ከሥጋ ደዌ በሽታ ለመንጻት የተመደበውን መሥዋዕት በድኽነቱ ምክንያት ማቅረብ ለማይችል ሰው የሚፈጸመው ሥርዓት ይህ ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ለመ​ን​ጻቱ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውን ነገር ለማ​ያ​ገኝ የለ​ምጽ ደዌ ላለ​በት ሰው ሕጉ ይህ ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ለመንጻቱ የሚያስፈልገውን ነገር ለማያገኝ የለምጽ ደዌ ላለበት ሰው ሕግ ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 14:32
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኛን በመዋረዳችን አስቦናልና፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥


ማናቸውም ሰው በሰውነቱ ቆዳ ላይ እባጭ ወይም ብጉር ወይም ቋቁቻ ቢታይ፥ በሰውነቱ ቆዳ እንደ ለምጽ ደዌ ቢሆን፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ካህናት ከሆኑት ከልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት።


“ንጹሕ ወይም ርኩስ መሆኑን ለመወሰን እንዲቻል፥ በበግ ጠጉር ልብስ ወይም በበፍታ ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከተለፋው ቆዳ በተሠራ በማናቸውም ነገር ላይ የሚወጣ የለምጽ ደዌ ሕግ ይህ ነው።”


“በስምንተኛውም ቀን ነውር የሌለባቸውን ሁለት ተባት ጠቦት፥ ነውር የሌለባትንም አንዲት የዓመት እንስት ጠቦት፥ ለእህሉም ቁርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ዘይትም ያለበትን አንድ የሎግ መስፈሪያ ይወስዳል።


“በመንጻቱ ቀን የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው ሕግ ይህ ይሆናል፤ ወደ ካህኑ ይወስዱታል።


“ነገር ግን ድሀ ቢሆን ይህንንም ለማቅረብ በቂ ገንዘብ ባይኖረው፥ እንዲያስተሰርይለት ለበደል መሥዋዕት እንዲወዘወዝ አንድ ጠቦት፥ ለእህልም ቁርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ አንድ እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ አንድ የሎግ መስፈሪያም ዘይት ይወስዳል።


አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውንም ከእህል ቁርባን ጋር ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፥ ካህኑም ለሚነጻው ሰው በጌታ ፊት ያስተሰርይለታል።


ጌታም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦


ዕውሮች ያያሉ፤ አንካሶች ይራመዳሉ፤ ለምጻሞችም ይነጻሉ፤ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፤ ሙታን ይነሣሉ፤ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች