ዘሌዋውያን 14:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 ካህኑም በእጁ መዳፍ ላይ ካለው ዘይት የሚነጻውን ሰው የቀኝ ጆሮውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግሩንም አውራ ጣት፥ የበደልም መሥዋዕት ደም ባረፈበት ስፍራ ላይ ያስነካዋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም28 ካህኑም በመዳፉ ከያዘው ዘይት ጥቂቱን ወስዶ የበደል መሥዋዕቱን ደም ባስነካበት ቦታ፣ ይኸውም የሚነጻውን ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣትና የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ያስነካ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 በእጁ ካለው ጥቂት ዘይት ወስዶ በበደል ስርየት መሥዋዕቱ ደም እንዳደረገው በሚነጻው ሰው በቀኝ ጆሮ የቀኝ እጁ አውራ ጣት መዳፍ ላይና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ያስነካዋል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 ካህኑም በእጁ ውስጥ ከአለው ዘይት የሚነጻውን ሰው የቀኝ ጆሮውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግሩንም አውራ ጣት የበደል መሥዋዕት ደም ባረፈበት ላይ ይቀባዋል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 ካህኑም በእጁ ውስጥ ካለው ዘይት የሚነጻውን ሰው የቀኝ ጆሮውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግሩንም አውራ ጣት የበደል መሥዋዕት ደም ባረፈበት ላይ ያስነካዋል። ምዕራፉን ተመልከት |