ዘሌዋውያን 14:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ካህኑም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን በመሠዊያው ላይ ያቀርባል፤ እንዲህም አድርጎ ካህኑ ያስተሰርይለታል፤ እርሱም ንጹሕ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ካህኑም ከእህል ቍርባኑ ጋራ በመሠዊያው ላይ በማቅረብ ያስተስርይለት፤ ሰውየውም ንጹሕ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 እርሱንም ከእህል መባ ጋር በመሠዊያው ላይ አኑሮ ያቃጥለዋል፤ በዚህ ዐይነት ካህኑ ያስተሰርይለታል፤ ያም ሰው ንጹሕ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ካህኑም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን በመሠዊያው ላይ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርባል፤ ካህኑም ያስተሰርይለታል፤ እርሱም ንጹሕ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ካህኑም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን በመሠዊያው ላይ ያቀርባል፥ ካህኑም ያስተሰርይለታል፤ እርሱም ንጹሕ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከት |