Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 14:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 “በስምንተኛውም ቀን ነውር የሌለባቸውን ሁለት ተባት ጠቦት፥ ነውር የሌለባትንም አንዲት የዓመት እንስት ጠቦት፥ ለእህሉም ቁርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ዘይትም ያለበትን አንድ የሎግ መስፈሪያ ይወስዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “በስምንተኛው ቀን እንከን የሌለባቸውን ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶችና ነውር የሌለባትን አንዲት የአንድ ዓመት እንስት በግ ያቅርብ፤ እንዲሁም ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሦስት ዐሥረኛ የላመ ዱቄት ያቅርብ፤ ደግሞ አንድ ሎግ ዘይት ያምጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “በስምንተኛውም ቀን ምንም ነውር የሌለባቸውን ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶችና አንድ ዓመት የሆናት አንዲት ቄብ ያምጣ፤ ከዚህም ጋር በወይራ ዘይት የተለወሰ ሦስት ኪሎ ግራም ዱቄትና የሊትር አንድ ሦስተኛ የሆነ የወይራ ዘይት ያምጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 “በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን፥ ዓመት የሞ​ላ​ቸ​ውን ሁለት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ት​ንም አን​ዲት የዓ​መት እን​ስት የበግ ጠቦት፥ ስለ እህ​ልም ቍር​ባን ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ፥ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት፥ አንድ ማሰሮ ዘይ​ትም ይወ​ስ​ዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በስምንተኛውም ቀን ነውር የሌለባቸውን ሁለት ተባት ጠቦት፥ ነውር የሌለባትንም አንዲት የዓመት እንስት ጠቦት፥ ስለ እህልም ቍርባን ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ አንድ የሎግ መስፈሪያም ዘይት ይወስዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 14:10
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ማናቸውም ሰው የእህል ቁርባን ለጌታ ሲያቀርብ ቁርባኑ ከመልካም ዱቄት ይሁን፤ ዘይትም ያፈስበታል፥ ዕጣንም ይጨምርበታል፤


እርሱም ለማንም እንዳይናገር አዘዘው፤ ነገር ግን፦ “ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ እንዳዘዘ መሥዋዕት አቅርብ፤” አለው።


“ለማንም አንድ ነገር እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ምስክር እንዲሆናቸው ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ስለ መንጻትህም ሙሴ ያዘዘውን መሥዋዕት አቅርብ” አለው።


ኢየሱስም “ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ሙሴ ያዘዘውን መባ አቅርብ” አለው።


“ነገር ግን ድሀ ቢሆን ይህንንም ለማቅረብ በቂ ገንዘብ ባይኖረው፥ እንዲያስተሰርይለት ለበደል መሥዋዕት እንዲወዘወዝ አንድ ጠቦት፥ ለእህልም ቁርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ አንድ እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ አንድ የሎግ መስፈሪያም ዘይት ይወስዳል።


ካህኑም ከሎግ መስፈሪያው ውስጥ ያለውን ዘይት ወስዶ በግራ እጁ መዳፍ ላይ ያፈስሰዋል።


ካህኑም አንዱን ተባት ጠቦት ይወስዳል፤ እርሱንም ስለ በደል መሥዋዕት ያቀርበዋል፥ ጎን ለጎንም ዘይቱ ያለበትን የሎግ መስፈሪያውን፤ እነርሱንም ስለ መወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ይወዘውዛቸዋል።


ነገር ግን ነውርና እድፍ እንደሌለው በግ ደም፥ በክርስቶስ ክቡር ደም ነው፥


እኔ ከሰማይ የወረደው ሕያው እንጀራ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘለዓለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።”


የእግዚአብሔር እንጀራ ከሰማይ የሚወርድ ለዓለምም ሕይወትን የሚሰጥ ነውና፤” አላቸው።


በማግሥቱ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ “እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።


የእህል ቁርባናቸውንም በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለአንድ ወይፈን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአውራውም በግ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ፥


ቁርባኑንም ለጌታ ያቅርብ፤ ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ነውርም የሌለባትን የአንድ ዓመት እንስት ጠቦት ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ነውርም የሌለበትን አውራ በግ ለአንድነት መሥዋዕት፥


የእህልም ቁርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ይሁን፤ ለመጠጥም ቁርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ የሆነ የወይን ጠጅ ይቅረብ።


በስምንተኛውም ቀን እንዲህ ሆነ፤ ሙሴ አሮንንና ልጆቹን የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ጠራ።


“ስለ ኃጢአትም መሥዋዕት የበግ ጠቦት ቢያቀርብ፥ ነውር የሌለባትን እንስት ያመጣል።


የምታቀርበውን የእህል ቁርባን ሁሉ በጨው ታጣፍጠዋለህ፤ የአምላክህንም የቃል ኪዳን ጨው ከእህል ቁርባንህ እንዳታጐድል፤ በቁርባንህ ሁሉ ላይ ጨው ታቀርባለህ።


“ማንኛውም እርሾ ያለበትን ነገርና ማርን፥ ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጋችሁ አታቃጥሉትምና ለጌታ የምታቀርቡት የእህል ቁርባን ሁሉ በእርሾ የተዘጋጀ አይሁን።


“የእርሱም ቁርባን ለሚቃጠል መሥዋዕት ከበጎች ወይም ከፍየሎች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርበዋል።


ከአንዱ ጠቦት ጋር አሥረኛ እጅ የኢፍ መስፈሪያ መልካም ዱቄት ከአራተኛ እጅ የኢን መስፈሪያ ተወቅጦ ከተጠለለ ዘይት ጋር የተለወሰ፥ ለመጠጥ ቁርባን የሚሆን ደግሞ አራተኛ እጅ የኢን መስፈሪያ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ።


የሚያነጻውም ካህን የሚነጻውን ሰውና እነዚህን ነገሮች በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በጌታ ፊት ያኖራቸዋል።


መባውም ለእህል ቁርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ ጐድጓዳ ሳሕን፤


“መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከበሬ መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በጌታ ፊት እንዲሠምርለት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች