ዘሌዋውያን 13:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)45 “የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው የሚለብሳቸው ልብሶች የተቀደዱ ይሁኑ፥ የራሱም ጠጉር የተጐሳቈለ ይሁን፥ ከንፈሩንም ይሸፍን፤ ርኩስ ርኩስ ነኝ እያለ ይጩኽ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም45 “እንዲህ ያለ ተላላፊ በሽታ ያለበት ሰው የተቀደደ ልብስ ይልበስ፤ ጠጕሩን ይግለጥ፤ እስከ አፍንጫውም ድረስ ተሸፋፍኖ ‘ርኩስ ነኝ! ርኩስ ነኝ!’ እያለ ይጩኽ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም45 “በዚህ ዐይነት የሥጋ ደዌ በሽታ ያለበት ሰው የተቀዳደደ ልብስ ይልበስ፤ ጠጒሩን አያበጥር፥ ከንፈሩን ይሸፍን፤ ከዚያም በኋላ ‘እኔ የረከስኩ ነኝ! የረከስኩ ነኝ!’ እያለ ይጩኽ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)45 “የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው ልብሱ የተቀደደ ይሁን፤ ራሱም የተገለጠ ይሁን፤ ከንፈሩንም ይሸፍን፤ ርኩስ ይባላል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)45 የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው ልብሱ የተቀደደ ይሁን፥ ራሱም የተገለጠ ይሁን፥ ከንፈሩንም ይሸፍን፤ ርኩስ ርኩስ ነኝ ይበል። ምዕራፉን ተመልከት |