Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 13:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ዳሩ ግን በቡሀነቱ ወይም በራሰ በራነቱ ነጣ ብሎ ቀላ ያለ ደዌ ቢኖርበት፥ እርሱ ከቡሀነቱ ወይም ከራሰ በራነቱ የወጣ የለምጽ ደዌ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ነገር ግን በመላጣው ወይም በበራው ላይ ነጣ ያለ ቀይ ቍስል ቢወጣበት፣ ያ ከመላጣው ወይም ከበራው የወጣ ተላላፊ በሽታ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ነገር ግን በራ በሆነው ራስ ወይም ግንባር ላይ ወደ ቀይነት ያደላ ነጭ ቊስል ቢታይበት እርሱ የሥጋ ደዌ በሽታ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 በቡ​ሀ​ነቱ ወይም በራሰ በራ​ነቱ ነጭ፥ ወይም ቀላ ያለ ደዌ ቢኖ​ር​በት፥ እርሱ ከቡ​ሀ​ነቱ ወይም ከራሰ በራ​ነቱ የወጣ ለምጽ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 በቡሀነቱ ወይም በራሰ በራነቱ ነጭ ወይም ቀላ ያለ ደዌ ቢኖርበት፥ እርሱ ከቡሀነቱ ወይም ከራሰ በራነቱ የወጣ ለምጽ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 13:42
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በብጉንጁም የቁስል ስፍራ ላይ ነጭ እባጭ ወይም ነጣ ብሎ ቀላ ያለ ቋቁቻ ቢወጣ፥ በካህኑ ዘንድ ይታያል።


ማናቸውም ሰው በሰውነቱ ቆዳ ላይ እባጭ ወይም ብጉር ወይም ቋቁቻ ቢታይ፥ በሰውነቱ ቆዳ እንደ ለምጽ ደዌ ቢሆን፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ካህናት ከሆኑት ከልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት።


ጠጉሩም ከግምባሩ ቢመለጥ እርሱ ራሰ በራ ነው፤ ነገር ግን ንጹሕ ነው።


ካህኑም ያየዋል፤ እነሆም፥ የደዌው እብጠት፥ በሰውነቱ ቆዳ ላይ የሆነ የለምጽ ደዌ መስሎ፥ በቡሀነቱ ወይም በራሰ በራነቱ ላይ ነጣ ብሎ ቀላ ያለ ቢሆን፥


ደዌውንም ያያል፤ እነሆም፥ ደዌው በቤቱ ግድግዳ ላይ አረንጓዴ ወይም ቀይ ሆኖ ቢዥጐረጐር፥ መልኩም ከግድግዳው ውጫዊ ገጽታ ዘልቆ ቢገባ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች