ዘሌዋውያን 13:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)37 ቈረቈሩ ግን መገታቱን ቢያይ፥ ጥቁርም ጠጉር ቢበቅልበት፥ ቈረቈሩ ድኖአል፤ እርሱም ንጹሕ ነው፤ ካህኑም፦ ንጹሕ ነው ይለዋል።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም37 ነገር ግን ቍስሉ በካህኑ አመለካከት ለውጥ ያላሳየ ከሆነና በውስጡ ጥቍር ጠጕር ካበቀለ ቍስሉ ድኗል፤ ሰውየው ነጽቷል፤ ካህኑም ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም37 ነገር ግን በካህኑ አመለካከት ቊስሉ ካልተስፋፋና ጤናማ ጠጒርም በቅሎበት ከተገኘ፥ ቊስሉ የተፈወሰ ስለ ሆነ፥ ንጹሕ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅለት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)37 ቈረቈሩ ግን ፊት እንደ ነበረ በቦታው ቢኖር፥ ጥቁርም ጠጕር ቢበቅልበት፥ ቈረቈሩ ሽሮአል፤ እርሱም ንጹሕ ነው፤ ካህኑም፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለዋል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)37 ቈረቈሩ ግን በዓይኑ ፊት እንደ ነበረ ቢሆን፥ ጥቁርም ጠጕር ቢበቅልበት፥ ቈረቈሩ ሽሮአል እርሱም ንጹሕ ነው፤ ካህኑም፦ ንጹሕ ነው ይለዋል። ምዕራፉን ተመልከት |