ዘሌዋውያን 13:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 ቋቁቻውም በስፍራው ላይ ቢቆም፥ በቆዳውም ላይ ባይሰፋ ነገር ግን ቢከስም፥ የቃጠሎው እባጭ ነው፤ የቃጠሎውም ጠባሳ ነውና ካህኑ፦ ንጹሕ ነው ይለዋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም28 ቋቍቻ ባለበት ከቈየና በቈዳው ላይ ካልተስፋፋ፣ ይልቁንም እየከሰመ ከሄደ፣ በቃጠሎው ሰበብ የተከሠተ ዕብጠት ነውና ካህኑ ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ፤ የቃጠሎው ጠባሳ እንጂ ሌላ አይደለም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 ነገር ግን ቊስሉ ያለበት ስፍራ ምንም ለውጥ ሳያሳይና ሳይስፋፋ የቀለም መለዋወጥ ብቻ ሆኖ ከተገኘ በእሳት ቃጠሎ ምክንያት የመጣ ጠባሳ ስለ ሆነ ያ ሰው ንጹሕ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅለት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 ቋቍቻውም በስፍራው ላይ ቢቆም፥ በቆዳውም ላይ ባይሰፋ፥ ነገር ግን ቢከስም፥ የትኩሳት እባጭ ነው፤ የትኩሳትም ጠባሳ ነውና ካህኑ፦ ‘ንጹሕ ነው’ ይለዋል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 ቍቁቻውም በስፍራው ላይ ቢቆም፥ በቁርበቱም ላይ ባይሰፋ ነገር ግን ቢከስም፥ የትኩሳት እባጭ ነው፤ የትኩሳትም ጠባሳ ነውና ካህኑ፦ ንጹሕ ነው ይለዋል፥ ምዕራፉን ተመልከት |