ዘሌዋውያን 12:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እርሱም በጌታ ፊት ያቀርበዋል ያስተሰርይላታልም፤ ከሚፈስሰውም ደምዋ ትነጻለች። ወንድ ወይም ሴት ለምትወልድ ሴት ሕጉ ይህ ነው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ያቅርበው፤ ያስተስርይላትም፤ ሴትዮዋም ከደሟ ፈሳሽ ትነጻለች። “ ‘ሴትዮዋ ወንድ ወይም ሴት ብትወልድ ሕጉ ይኸው ነው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ካህኑም ስጦታዋን ተቀብሎ ለእግዚአብሔር ያቀርባል፤ የደም መፍሰስ ርኵሰትዋ ተወግዶ የምትነጻበትንም ሥርዓት ይፈጽማል፤ ከዚያም በኋላ የነጻች ትሆናለች፤ ይህም እንግዲህ ወንድ ወይም ሴት ከወለደች በኋላ የምትፈጽመው ሕግ ሆኖ ይኖራል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበዋል፤ ያስተሰርይላትማል፤ ከደምዋም ፈሳሽ ትነጻለች። ወንድ ወይም ሴት ለምትወልድ ሴት ሕጉ ይህ ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ያቀርበዋል ያስተሰርይላትማል፤ ከደምዋም ፈሳሽ ትነጻለች። ወንድ ወይም ሴት ለምትወልድ ሴት ሕጉ ይህ ነው። ምዕራፉን ተመልከት |