Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 11:46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 የእንስሳና የወፍ፥ በውኃም ውስጥ የሚንቀሳቀሱና በምድር ላይ የሚርመሰመሱ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ሕግ ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 “ ‘እንስሳትንና አዕዋፍን፣ በውሃ ውስጥ የሚኖሩትንና ምድር ለምድር የሚንቀሳቀሱትን ፍጥረታት ሁሉ በሚመለከት የተሰጠ ሕግ ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 “ይህ እንግዲህ በውሃ ውስጥ ስለሚኖሩና በምድር ላይ ስለሚንቀሳቀሱ ስለ እንስሶችና ወፎች ሁሉ የተሰጠ ሕግ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 “የእ​ን​ስ​ሳና የወፍ፥ በው​ኃ​ውም ውስጥ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የፍ​ጥ​ረት ሁሉ፥ በም​ድ​ርም ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የፍ​ጥ​ረት ሁሉ ሕግ ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 የእንስሳና የወፍ፥ በውኃም ውስጥ የሚንቀሳቀስ የፍጥረት ሁሉ፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀስ የፍጥረት ሁሉ ሕግ ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 11:46
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔርም አለ፦ “ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ፥ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር በታች ይብረሩ።”


እግዚእብሔርም ታላላቆች አንበሪዎችን፥ ውኃይቱ እንደ ወገኑ ያስገኘቻቸውን ተንቀሳቃሾቹን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ፥ እንደ ወገኑ የሚበሩትንም ወፎች ሁሉ ፈጠረ፥ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።


የቤቱ ሕግ ይህ ነው፤ በተራራው ራስ ላይ በዙሪያው ያለው ስፍራ ሁሉ የተቀደስ ይሆናል። እነሆ፥ የቤቱ ሕግ ይህ ነው።


እኔ አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ ጌታ ነኝ፤ ስለዚህ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ።”


በዚህም በርኩስና በንጹሕ መካከል፥ በሚበላና በማይበላ ሕይወት ባለው ፍጥረት መካከል ለመለየት ነው።


“ይህ ሕግ ለሁሉም ዓይነት የለምጽ ደዌ፥ ለቈረቈርም፥


ፈሳሽ ነገር ላለበት ሰው፥ ዘሩም ለሚፈስስበት በእርሱም ምክንያት ለሚረክሰው ሰው ሕጉ ይህ ነው፤


የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቁርባን፥ የኃጢአትና የበደል መሥዋዕት፥ የቅድስናና የአንድነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች