Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 11:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በእናንተም ዘንድ የተጸየፉ ይሆናሉ፤ ሥጋቸውንም አትብሉ፥ በድናቸውንም ተጸየፉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በእናንተ ዘንድ አስጸያፊ ስለ ሆኑ ሥጋቸውን አትብሉ፤ በድናቸውንም ትጸየፋላችሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እንደነዚህ ያሉት እንስሶች በእናንተ ዘንድ የረከሱ ሆነው መቈጠር አለባቸው፤ እነርሱን መብላት ቀርቶ በድናቸውን መንካት እንኳ የለባችሁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በእ​ና​ን​ተም ዘንድ የተ​ጸ​የፉ ይሆ​ናሉ። ሥጋ​ቸ​ው​ንም አት​በ​ሉም፤ በድ​ና​ቸ​ው​ንም ትጸ​የ​ፋ​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በእናንተም ዘንድ የተጸየፉ ይሆናሉ፤ ሥጋቸውንም አትበሉም፥ በድናቸውንም ትጸየፋላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 11:11
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነ እንስሳም ሁለት ሁለት ተባዕትና እንስት፤


ከሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት እያደረግህ በምድር ላይ ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትወስዳለህ።


ነገር ግን በውኆች ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ፥ በውኆች ውስጥም በሕይወት ከሚኖሩ ነፍሳት፥ በባሕሮችና በወንዞች ውስጥ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸውን ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው።


በውኃ ውስጥ የሚኖሩ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው።


“ከወፎችም ወገን የምትጸየፉአቸው እነዚህ ናቸው፤ አይበሉም፤ የተጸየፉ ናቸው፤ ንስር፥ ገዲ፥ ዓሣ አውጭ፥


“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብላችሁ ተናገሩ፦ በሕይወት ከሚኖሩ ከምድር እንስሶች ሁሉ የምትበሉአቸው እነዚህ ናቸው።


ማንም ሰው ማንኛውንም ርኩስ ነገር ማለትም የረከሰ አውሬ በድን፥ ወይም የረከሰ ከብት በድን፥ ወይም በደረቱ እየተሳበ የሚርመሰመስ የረከሰ ፍጥረት በድን ሳይታወቀው ቢነካ፥ እርሱ ርኩስ ይሆናል፤ በደለኛም ነው፤


የምትበሏቸው እንስሳት እነዚህ ናቸው፤ በሬ፥ በግ፥ ፍየል፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች