Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 10:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ሙሴም የኃጢአት መሥዋዕት ስለ ሆነው ፍየል አጥብቆ ጠየቀ፥ እነሆም ተቃጥሎ ነበር፤ ሙሴም የተረፉትን የአሮንን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ ብሎ ተቆጣ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ሙሴ ለኀጢአት መሥዋዕት የሚቀርበውን ፍየል አጥብቆ ፈለገ፤ መቃጠሉንም በተረዳ ጊዜ የተረፉትን የአሮንን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን ተቈጣቸው፤ እንዲህም አላቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሙሴ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት በመሆን ቀርቦ የነበረውን ፍየል ምን እንዳደረጉት በጠየቀ ጊዜ ተቃጥሎ እንደ ነበር ተረዳ፤ ይህም ነገር በአልዓዛርና በኢታማር ላይ ሙሴን ስላስቈጣው እንዲህ ሲል ጠየቀ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ሙሴም የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል እጅግ ፈለ​ገው፤ በፈ​ለ​ገ​ውም ጊዜ እነሆ ተቃ​ጥሎ ነበር፤ ሙሴም የቀ​ሩ​ትን የአ​ሮ​ንን ልጆች አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን ተቈ​ጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ሙሴም የኃጢያቱን መሥዋዕት ፍየል እጅግ ፈለገው፥ እነሆም ተቃጥሎ ነበር፤ ሙሴም የቀሩትን የአሮንን ልጆች አልአዛርንና ኢታምርን ተቆጥቶ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 10:16
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፦ ‘ለኃጢአት መሥዋዕት አውራ ፍየልን፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን አንድ ዓመት የሆናቸውን እምቦሳና ጠቦትን፥


ከዚያም በኋላ የሕዝቡን ቁርባን አቀረበ፤ ስለ ሕዝቡ ለኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን ፍየል ወስዶ አረደው፥ ስለ ኃጢአትም እንደ ፊተኛው የኃጢአት መሥዋዕት ሠዋው።


ተቆጡ፥ ኃጢአትን ግን አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፤


ኢየሱስም ይህን ሲያይ ተቆጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “ሕፃናት ወደ እኔ ይምጡ፤ አትከልክሏቸው፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና።


ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ፥ ዙሪያውን በቁጣ ተመለከተና ሰውየውን፦ “እጅህን ዘርጋ፤” አለው። እርሱም ዘረጋ፤ እጁም ዳነች።


እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወንድሙን የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙን ‘የማያስብ’ የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ‘ደደብ’ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።


ሙሴም በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበረ።


ነገር ግን በመቅደሱ ውስጥ ለማስተስረያ እንዲሆን ከደሙ ወደ መገናኛው ድንኳን የሚገባው የኃጢአት መሥዋዕት ሁሉ አይበላም፤ በእሳት ይቃጠላል።”


ለኃጢአት የሚሠዋው ካህን ይበላዋል፤ በመገናኛው ድንኳን ዙሪያ ባለው አደባባይ በተቀደሰ ስፍራ ይበላል።


በእርሾ ቦክቶ አይጋገርም። እርሱን በእሳት የሚቀርብ ቁርባኔ አድርጌ ድርሻቸው እንዲሆን ሰጠሁ፤ እርሱም እንደ ኃጢአትና እንደ በደል መሥዋዕት እጅግ የተቀደሰ ነው።


የአቢሹዓ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ፥ የኤልዓዛር ልጅ፥ የታላቁ ካህን የአሮን ልጅ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች