ዘሌዋውያን 10:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 የአሮንም ልጆች ናዳብና አብዩድ እያንዳንዳቸው ጥናቸውን ወስደው እሳት አደረጉበት፥ በላዩም ዕጣን አኖሩበት፥ በጌታም ፊት እርሱ ያላዘዛቸውን ያልተፈቀደውን እሳት አቀረቡ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 የአሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ እያንዳንዳቸው ጥናዎቻቸውን ወስደው ፍም አደረጉባቸው፤ ዕጣንም ጨመሩባቸው፤ እርሱ ያላዘዛቸውን፣ ያልተፈቀደውን እሳት በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ናዳብና አቢሁ የተባሉት ሁለቱ የአሮን ልጆች እያንዳንዳቸው ጥናቸውን ወስደው፥ የእሳት ፍም ጭረው ጨመሩበት፤ በእርሱም ላይ ዕጣን አድርገው ወደ እግዚአብሔር አቀረቡ፤ ያን ዐይነት እሳት ያቀርቡ ዘንድ እግዚአብሔር ስላላዘዛቸው፤ ያ እሳቱ የተቀደሰ አልነበረም፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 የአሮንም ልጆች ናዳብና አብዩድ በየራሳቸው ጥናውን ወስደው እሳት አደረጉበት፤ በላዩም ዕጣን ጨመሩበት፤ በእግዚአብሔርም ፊት እግዚአብሔር ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት አቀረቡ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 የአሮንም ልጆች ናዳብና አብዩድ በየራሳቸው ጥናውን ወስደው እሳት አደረጉበት፥ በላዩም ዕጣን አኖሩበት፥ በእግዚአብሔርም ፊት እርሱ ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት አቀረቡ። ምዕራፉን ተመልከት |