ዘሌዋውያን 1:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ክንፎቹንም ይዞ በመነጠል ይቀድደዋል እንጂ አይከፍለውም። ካህኑም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ያቃጥለዋል፤ እርሱም በጌታ ዘንድ መዓዛው ያማረ ሽታ የሆነ፥ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን፥ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 በክንፎቹ በኩል ለሁለት ይሰንጥቀው፤ ነገር ግን ጨርሶ አያለያየው፤ ካህኑም በመሠዊያው ላይ በሚነድደው ዕንጨት ላይ ያቃጥለው፤ ይህም በእሳት የሚቀርብ፣ ሽታውም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ክንፎቹንም ይዞ ሳይከፋፍል አካሉን በመከፋፈል በመሠዊያው ላይ በሚገኘው እሳት ያቃጥለው፤ የዚህ ዐይነቱ መሥዋዕት መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ከክንፎቹም ይሰብረዋል፤ ነገር ግን አይለየውም። ካህኑም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በዕንጨቱ ላይ ያኖረዋል፤ መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍርባን ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 በክንፎቹም ይቀድደዋል፥ ነገር ግን አይከፍለውም። ካህኑም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ያቃጥለዋል፤ የሚቃጠል መሥዋዕት የእሳት ቍርባን በእግዚአብሔር ዘንድ ጣፋጭ ሽታ ነው። ምዕራፉን ተመልከት |