Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሰቈቃወ 5:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አባቶቻችን ኃጢአትን ሠሩ ዛሬም የሉም፥ እኛም በደላቸውን ተሸከምን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 አባቶቻችን ኀጢአት ሠርተው ዐለፉ፤ እኛም የእነርሱን ቅጣት ተሸከምን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 አባቶቻችን ኃጢአት ሠርተው አለፉ፤ እኛ ግን የእነርሱን ኃጢአት እንሸከማለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አባ​ቶ​ቻ​ችን ኀጢ​አ​ትን ሠሩ፤ ዛሬም የሉም፤ እኛም በደ​ላ​ቸ​ውን ተሸ​ከ​ምን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አባቶቻችን ኃጢአትን ሠሩ ዛሬም የሉም፥ እኛም በደላቸውን ተሸከምን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሰቈቃወ 5:7
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያ ዘመን ሰዎች ዳግመኛ እንዲህ አይሉም፦ ‘አባቶች የሚጎመዝዝ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች ጠረሱ፤’


እናንተም ከአባቶቻችሁ ይልቅ ክፉ አድርጋችኋል፤ እነሆም፥ ሁላችሁ እንደ ክፉ ልባችሁ እልከኝነት ሄዳችኋል እኔንም አልሰማችሁም።


አባቶች ጎምዛዛ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች አጠረሰ፥ ብላችሁ ስለ እስራኤል ምድር የምትመስሉት ምሳሌ ምንድነው?


አቤቱ! በአንተ ላይ ኃጢአትን ሠርተናልና ክፋታችንንና የአባቶቻችንን በደል እናውቃለን።


አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም፤ እኔ ጌታ አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።”


አባታቸው ያዕቆብም፥ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ ኧረ ምን ጉድ ነው የመጣብኝ!” አላቸው።


አባቶቻችሁ ወዴት ናቸው? ነቢያትስ ለዘለዓለም በሕይወት መኖር የሚችሉ ይመስላችኋልን?


ስለምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኃጢአቴንስ ስለምን አታስወግድልኝም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፥ ትፈልገኛለህ፥ እኔ ግን የለሁም።”


የሚያየኝ ሰው ዐይን ከእንግዲህ ወዲህ አያየኝም፥ ዓይንህ በእኔ ላይ ይሆናል፥ እኔም አልገኝም።


እነርሱ ግን መልሰው፥ “እኛ አገልጋዮችህ በከነዓን አገር ከሚኖር ከአንድ ሰው የተወለድን ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን። ትንሹ ወንድማችን አባታችን ዘንድ ሲሆን፥ አንዱ ግን የለም” አሉት።


‘ጌታ ታጋሽና ጽኑ ፍቅሩ የበዛ፥ በደልንና መተላለፍን ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን በደል እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው።’


አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ‘አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተው ነው፥ ይላል ጌታ፥ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ አገለገሉአቸውም ሰገዱላቸውም፥ እነርሱም ትተውኛል፥ ሕጌንም አልጠበቁም፤


ክፋትሽንና ርኩሰነትሽን መሸከም አለብሽ፥ ይላል ጌታ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች