Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሰቈቃወ 5:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ፥ ተመልከት ስድባችንንም እይ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ሆይ፤ በእኛ ላይ የደረሰውን ዐስብ፤ ውርደታችንን እይ፤ ተመልከትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር ሆይ! በእኛ ላይ የደረሰውን አስብ፤ ውርደታችንንም ተመልከት!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አቤቱ፥ የሆ​ነ​ብ​ንን ዐስብ፤ ተመ​ል​ከት ስድ​ባ​ች​ን​ንም እይ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ፥ ተመልከት ስድባችንንም እይ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሰቈቃወ 5:1
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነርሱም፦ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ትሩፋን በታላቅ መከራና በመሰደብ ይገኛሉ፤ የኢየሩሳሌም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ።


ለአገልጋይህ ለሙሴ እንዲህ ብለህ ያዘዝኸውን ቃል እባክህ አስብ። “ታማኞች ካልሆናችሁ በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤


ይሁዳም፦ “የተሸካሚዎች ኃይል ደክሟል፥ ፍርስራሹም ብዙ ነው፤ ቅጥሩን መሥራት አንችልም” አለ።


ከጭቃ እንደሠራኸኝ አስታውስ፥ ወደ ትቢያም ትመልሰኛለህን?


“ሕይወቴ እስትንፋስ እንደሆነ አስታውስ፥ ዓይኔ መልካም ነገርን ከእንግዲህ ወዲህ አያይም።


ሕግህን አልረሳሁምና ችግሬን ተመልከት አድነኝም።


ይህንንም አስታውስ፥ ጠላት በጌታ ተሳለቀ፥ አላዋቂ ሕዝብም በስምህ ቀለደ።


አቤቱ፥ የተዘባበቱብህን መዘባበታቸውን ለጎረቤቶቻችን ሰባት እጥፍ በብብታቸው ክፈላቸው።


ለጎረቤቶቻችንም ስድብ ሆንን፥ በዙሪያችንም ላሉ መሳቂያና መሳለቂያ።


ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ዘብ ጠባቂዎችን በቅጥሮችሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንም ሆነ ሌሊት ከቶ ዝም አይሉም። እናንት ወደ ጌታ አቤት፤ አቤት የምትሉ፤ ፈጽሞ አትረፉ፤


አቤቱ! አንተ ታውቃለህ፤ አስታውሰኝ ጐብኘኝም፥ የሚያሳድዱኝንም ተበቀልልኝ፤ ቁጣህንም ከማዘግየትህ የተነሣ እንዳታጠፋኝ፤ ስለ አንተ ስድብን እንደ ታገሥሁ እወቅ።


ስድብን ስለ ሰማን አፍረናል፤ ባዕዳን ሰዎችም በጌታ ቤት ውስጥ ወዳሉት ወደ ተቀደሱ ስፍራዎች ገብተዋልና ውርደት ፊታችንን ሸፍኖታል።


ካፍ። ሕዝብዋ ሁሉ እየጮኹ ያለቅሳሉ እንጀራም ይፈልጋሉ፥ ሰውነታቸውን ለማበርታት የከበረ ሀብታቸውን ስለ መብል ሰጥተዋል፥ አቤቱ፥ ተጐሳቁያለሁና እይ፥ ተመልከትም።


ሬስ። አቤቱ፥ ተጨንቄአለሁና፥ አንጀቴም ታውኮብኛልና ተመልከት፥ ዓመፃን ፈጽሞ አድርጌአለሁና ልቤ በውስጤ ተገላበጠብኝ፥ በሜዳ ሰይፍ ልጆቼን አጠፋ በቤትም ሞት አለ።


ጤት። አደፍዋ በልብስዋ ዘርፍ ነበረ፥ ፍጻሜዋን አላሰበችም፥ ስለዚህ በድንቅ ተዋርዳለች፥ የሚያጽናናትም የለም፥ አቤቱ፥ ጠላት ከፍ ከፍ ብሏልና መከራዬን ተመልከት።


ሳምኬት። መንገድ አላፊዎች ሁሉ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻልና፦ በውኑ የውበት ፍጻሜና የምድር ሁሉ ደስታ የሚሉአት ከተማ ይህች ናትን? እያሉ፥ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍዋጫሉ፥ ራሳቸውንም ያነቃንቃሉ።


ሬስ። አቤቱ፥ እይ፥ በማን ላይ እንደዚህ እንዳደረግህ ተመልከት። በውኑ ሴቶች ፍሬያቸውን፥ ያቀማጠሉአቸውን ሕፃናት፥ ይበላሉን? በውኑ ካህኑና ነቢዩ በጌታ መቅደስ ውስጥ ይገደላሉን?


ዛይ። መከራዬንና ችግሬን እሬትንና ሐሞትን አስብ።


ሳን። አቤቱ፥ ስድባቸውንና በእኔ ላይ ያለውን አሳባቸውን ሁሉ፥


ጌታ ሆይ፥ ዝናህን ሰምቻለሁ፥ በሥራህም ጌታ ሆይ ፈራሁ፥ በዓመታት መካከል አድሰው፥ በዓመታት መካከል አስታውቀው፥ በቁጣ ጊዜ ምሕረትን አስብ።


ኢየሱስንም “ጌታ ሆይ! በመንግሥትህ ስትመጣ አስበኝ፤” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች