Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሰቈቃወ 4:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ታው። የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የበደልሽ ቅጣት ተፈጸመ፥ ከእንግዲህ ወዲህ አያስማርክሽም። የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፥ በደልሽን ይቀጣል፥ ኃጢአትሽን ይገልጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ቅጣትሽ ያበቃል፤ እርሱም የስደትሽን ዘመን አያራዝምም፤ ነገር ግን አንቺ የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፤ ኀጢአትሽን ይቀጣል፤ ክፋትሽንም ይፋ ያወጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! የበደላችሁ ቅጣት አብቅቶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ በስደት እንድትኖሩ አያደርጋችሁም፤ ነገር ግን የኤዶም ሕዝብ ሆይ! የእናንተን በደል ይቀጣል፤ ኃጢአታችሁንም ያጋልጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ታው። የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሆይ፥ በደ​ልሽ ተፈ​ጸመ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​ስ​ማ​ር​ክ​ሽም። የኤ​ዶ​ም​ያስ ሴት ልጅ ሆይ፥ በደ​ል​ሽን ይጐ​በ​ኘ​ዋል፤ ኀጢ​አ​ት​ሽ​ንም ይገ​ል​ጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ታው። የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የበደልሽ ቅጣት ተፈጸመ፥ ከእንግዲህ ወዲህ አያስማርክሽም። የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፥ በደልሽን ይቀጣል፥ ኃጢአትሽን ይገልጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሰቈቃወ 4:22
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፤ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፥ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፥ ከጌታም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርሷ ጩኹ።


እንደትሩፍ የተውኳቸውን እነዚያን ይቅር እላቸዋለሁና በዚያን ወራት በዚያም ዘመን፥ ይላል ጌታ፥ የእስራኤል በደል የይሁዳም ኃጢአት ይፈለጋል ነገር ግን በዚያ ምንም አይገኝም።


አቤቱ፥ በኢየሩሳሌም ቀን የኤዶምን ልጆች አስብ፦ እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ ያሉአትን።


ኤዶም፦ “እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን” ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ የክፋት አገር፥ ጌታ ለዘለዓለም የተቆጣው ሕዝብ ብለው ይጠሩአቸዋል።”


መቅደሴም ለዘለዓለም በመካከላቸው በሆነ ጊዜ፥ እስራኤልን የቀደስኩ እኔ ጌታ እንደሆንሁ አሕዛብ ያውቃሉ።


ሳን። በዖፅ ምድር የምትኖሪ የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ ሐሤትም አድርጊ፥ ጽዋው ደግሞ ወደ አንቺ ያልፋል፥ አንቺም ትሰክሪአለሽ ትራቈቻለሽም።


ዋው። የማንም እጅ ሳይወድቅባት ድንገት ከተገለበጠች ከሰዶም ኃጢአት ይልቅ የወገኔ ሴት ልጅ ኃጢአት በዛች።


በእኔም ላይ ከሠሩት ከበደላቸው ኃጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ፤ በእኔም ላይ ያመፁትንና የሠሩትን የበደላቸውን ኃጢአት ሁሉ ይቅር እላለሁ።


ለእነርሱም ከማደርገው በጎነት አልመለስም ስል፥ ከእነርሱ ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ከእኔም ዘንድ ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ።


ከዚያ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ግፍ፥ በዳርቻሽም ውስጥ ጉስቁልናና ቅጥቃጤ አይሰማም፤ ቅጥርሽን መዳን በሮችሽንም ምስጋና ብለሽ ትጠሪያለሽ።


ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፥ ኃይልሽን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ።


የይሁዳን ምርኮና የእስራኤልንም ምርኮ እመልሳለሁ፥ ቀድሞም እንደ ነበሩ አድርጌ እሠራቸዋለሁ።


እኔ ግን ዔሳውን ዐራቈትሁት፥ የመሸሸጊያውንም ስፍራዎች ገለጥሁ፥ እርሱም ለመሸሸግ አይችልም፤ ዘሩም ወንድሞቹም ጎረቤቶቹም ጠፍተዋል እርሱም የለም።


በሩቅ ያለው በቸነፈር ይሞታል፥ በቅርብ ያለውም በሰይፍ ይወድቃል፥ በሕይወት የተረፈውና የዳነውም በራብ ይሞታል፥ መዓቴን በእነርሱ ላይ እፈጽማለሁ።


ዔሳውን ግን ጠላሁት፤ ተራራውን አጠፋሁ፥ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮች ሰጠኋቸው።


በወንድምህ በያዕቆብ ላይ ስለተደረገው ግፍ እፍረትን ትከናነባለህ፤ ለዘለዓለምም ትጠፋለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች