ሰቈቃወ 2:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ዮድ። የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፥ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፥ ማቅም ታጠቁ፥ የኢየሩሳሌም ደናግል ራሳቸውን ወደ ምድር አዘነበሉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች፣ በምድር ላይ በዝምታ ተቀምጠዋል፤ በራሳቸው ላይ ትቢያ ነሰነሱ፤ ማቅም ለበሱ፤ የኢየሩሳሌም ወጣት ሴቶች፣ ራሳቸውን ወደ ምድር ዝቅ አደረጉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 የኢየሩሳሌም ከተማ ሽማግሌዎች ጸጥ ብለው በምድር ላይ ተቀመጡ፤ እነርሱ በራሳቸው ላይ ትቢያ ነስንሰው ማቅ ለበሱ፤ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች አንገታቸውን ደፉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ዮድ። የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፤ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፤ ማቅም ታጠቁ፤ በኢየሩሳሌም መሳፍንቱንና ደናግሉን ወደ ምድር አወረዷቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ዮድ። የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፥ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፥ ማቅም ታጠቁ፥ የኢየሩሳሌም ደናግል ራሳቸውን ወደ ምድር አዘነበሉ። ምዕራፉን ተመልከት |