ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ዮዲት 8:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 የሰው ልብ ጥልቀት ማግኘት አትችሉም፥ በአእምሮው የሚያስበውንም መያዝ አትችሉም፥ ይህን ሁሉ የሠራውን እግዚአብሔርን እንዴት ትመረምራላችሁ? ሐሳቡን ማወቅ ወይም ማስተዋል እንዴት ይሆንላችኋል? ወንድሞቼ ሆይ አይሆንም፥ ጌታ አምላካችንን አታስቆጡት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 በሰው ልቡና ያለ ረቂቅ ምሥጢርን የማታውቁ፥ የልቡናውንም አሳብ የማታስተውሉ ይህን ሁሉ ያደረገ እግዚአብሔርን እንዴት ትመረምራላችሁ? ልቡናውንስ መርምራችሁ ታውቁ ዘንድ እንዴት ትወዳላችሁ? ምክሩንስ መርምራችሁ ታገኙ ዘንድ እንዴት ትመረምራላችሁ? ወንድሞች ሆይ፥ ለእናንተ አግባባችሁ አይደለም፤ አምላካችን እግዚአብሔርንም አታሳዝኑት። ምዕራፉን ተመልከት |