ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ዮዲት 8:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 እነርሱም ወደ እርሷ መጡ፥ እርሷም እንዲህ አለቻቸው፦ “የቤቱሊያ ነዋሪዎች ገዢዎች ሆይ ስሙኝ! በዚህ ቀን በሕዝቡ ፊት የተናገራችሁት ንግግር ልክ አይደለም፤ በእግዚብአብሔርና በእናንተ መካከልም ይህን መሐላ አቆማችሁ፥ ጌታ ባይረዳችሁ ከተማይቱን ለጠላቶቻችን አሳልፋችሁ እንደምትሰጡ ተናገራችሁ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 እነርሱም ወደ እርስዋ መጡ፤ እርስዋም “ዛሬ በሕዝቡ ፊት የተናገራችሁት በጎ ነገር አይደለምና በቤጤልዋ የሚኖሩ ሰዎች ሹሞች ሆይ! ስሙኝ እግዚአብሔር በእነዚህ በአምስቱ ቀኖች ባይረዳችሁ ሀገራችሁን ለጠላቶቻችሁ አሳልፋችሁ ትሰጡ ዘንድ በእግዚአብሔርና በእናንተ መካከል የተማማላችሁትን መሐላ በዚህ አጸናችሁ። ምዕራፉን ተመልከት |