ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ዮዲት 7:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 የኤሳው ልጆችና የአሞን ልጆች ወጥተው በዶታይም ትይዩ ባለው ተራራማ አገር ሰፈሩ፤ ከእነሱም አንዳንዶቹን በሞኹር ወንዝ አጠገብ በኩሲ አቅራቢያ ወዳለው ወደ ደቡብና ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ወደ ኤግሬቤ ላኩ፤ የቀሩት የአሦር ወታደሮች ሜዳ ላይ ሰፈሩ፥ ምድርን በሙሉ ሸፈኗት፤ ድንኳኖቻቸውና ጓዛቸው እጅግ ሰፊ ቦታ ያዘ፥ እጅግም ብዙ ሆኑ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 የኤሳውና የአሞን ልጆችም ወጥተው በዶታይም አንጻር ባሉ ተራሮች ሰፈሩ፤ ከእነርሱም በምኩር ወንዝ ባለ በኩሲ አጠገብ ባለ በኤቄሬቢን አንጻር ወደ ደቡብና ወደ ምሥራቅ ሰዎችን ላኩ። የቀሩት የአሦር ሠራዊቶች ግን በምድረ በዳ ሰፈሩ፤ ሀገሩንም ሁሉ አለበሱት፤ ከዚህም በኋላ ጓዛቸውን ከእነርሱ የሚበዛ የሌለ ሠራዊታቸውንና ብዙ ገንዘባቸውን አጓዙ። ምዕራፉን ተመልከት |