ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ዮዲት 7:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ምክንያቱም የቤቱሊያ ነዋሪዎች ውኃ የሚቀዱት ከዚህ ነው፤ ውኃ ጥም ይገድላቸዋል፥ ስለዚህ ከተማቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ፤ በዚያን ጊዜ እኛና ሕዝቡ ወደ ተራራው ጫፍ አጠገብ እንወጣና ከከተማው ማንም ሰው እንዳይወጣ እንጠብቃለን። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 በቤጤልዋ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ከዚህ ውኃ ስለሚቀዱ ውኃ ጥም ይገድላቸዋል፤ ሀገራቸውንም ለአንተ ያሰገዛሉ፤ ሠራዊቶቻችንና እኛም ላንባቸው ቅርብ ወደ ሆነ ቦታ ወደ ኮረብታቸውም ራስ እንወጣለን ካንባቸው አንድ ሰው ስንኳ የሚወጣ እንዳይኖር በዚያ ሰፍረን እንጠብቃቸዋለን። ምዕራፉን ተመልከት |