ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ዮዲት 4:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 መሠዊያውንም ማቅ አለበሱ፤ ልጆቻቸውና ሚስቶቻቸው እንዳይዘረፉ፤ የወረሱአቸው ከተሞቻቸው እንዳይደመሰሱ፤ የተቀደሰው ቦታ በአረመኔዎች እንዳይረክስና እንዳይዋረድ ወደ እግዚአብሔር አጥብቀው ባንድነት አለቀሱ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ልጆቻቸውን እንዳይነጠቁ፥ ሚስቶቻቸውን እንዳይማረኩ፥ የርስታቸው ከተሞችም እንዳይጠፉ፥ መቅደሳቸውንም እንዳያረክሱ፥ ለአሕዛብም መዘበቻ እንዳያደርጉት ወደ እስራኤል አምላክ በአንድነት ፈጽመው ጮኹ። ምዕራፉን ተመልከት |