ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ዮዲት 1:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ነገር ግን በምድሪቱ የሚኖሩ ሁሉ የአሦርን ንጉሥ የናቡከደነፆርን ቃል ንቀው ከእሱ ጋር በጦርነት ላይ ለመሰለፍ እንቢ አሉ፤ አልፈሩትምና፥ እንደ አንድ ሰው ቆጥረዉታልና፤ መልክተኞቹንም ባዶ እጃቸውንና አዋርደው ከፊታቸው መለሱአቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 በምድር የሚኖሩ ሁሉ የፋርስ ንጉሥ የናቡከደነፆርን ትእዛዝ እንቢ አሉ፤ ከእርሱም ጋር ወደ ጦር አልሄዱም። አልፈሩትምና በፊታቸው እንደ አንድ ሰው ሆኗልና። መልእክተኞቹም ባዶአቸውን በውርደት ከፊታቸው ተመለሱ። ምዕራፉን ተመልከት |