መሳፍንት 9:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)36 ገዓል ባያቸው ጊዜ ዜቡልን፥ “ተመልከት፤ ከተራራው ጫፍ ሕዝብ እየወረደ ነው” አለው። ዜቡልም መልሶ፥ “የተራሮች ጥላ ሰዎች መስሎ ተሳስተህ ነው” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም36 ገዓል ባያቸው ጊዜ ዜቡልን፣ “ተመልከት፤ ከተራራው ጫፍ ሕዝብ እየወረደ ነው” አለው። ዜቡልም መልሶ፣ “የተራሮች ጥላ ሰዎች መስሎ ተሳስተህ” ነው አለው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም36 ጋዓልም እነርሱን አይቶ ዘቡልን “ተመልከት! ሰዎች ከተራራው ጫፍ ላይ እየወረዱ ነው!” አለው። ዘቡልም “እነርሱ በተራሮች ላይ የሚታዩ ጥላዎች እንጂ ሰዎች አይደሉም” ሲል መለሰለት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)36 የአቤድ ልጅ ገዓልም ሕዝቡን ባየ ጊዜ ዜቡልን፥ “እነሆ፥ ከተራሮች ራስ ሕዝብ ይወርዳል” አለው። ዜቡልም፥ “ሰዎችን የሚመስለውን የተራሮችን ጥላ ታያለህ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)36 ገዓልም ሕዝቡን ባየ ጊዜ ዜቡልን፦ እነሆ፥ ከተራሮች ራስ ሕዝብ ይወርዳል አለው። ዜቡልም፦ ሰዎች የሚመስለውን የተራሮችን ጥላ ታያለህ አለው። ምዕራፉን ተመልከት |