መሳፍንት 9:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 የሴኬም ነዋሪዎችም አቤሜሌክን ሸምቀው የሚጠባበቁትን ሰዎች መደቡ፤ ሰዎቹም እርሱን በመጠባበቅ ላይ ሳሉ በዚያ የሚያልፈውን ሁሉ ዘረፉ፤ ወሬውም ለአቤሜሌክ ደረሰው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 የሴኬም ገዦችም አቢሜሌክን ሸምቀው የሚጠባበቁትን ሰዎች መደቡ፤ ሰዎቹም እርሱን በመጠባበቅ ላይ ሳሉ በዚያ የሚያልፈውን ሁሉ ዘረፉ፤ ወሬውም ለአቢሜሌክ ደረሰው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 የሴኬም ኗሪዎች በአቤሜሌክ ላይ በጠላትነት ተነሥተው ጥቂት ሰዎችን መርጠው በተራሮች ጫፍ ላይ ሸመቁ፤ በመንገዳቸው የሚያልፈውን ሰው ሁሉ ዘረፉ፤ አቤሜሌክም ይህን ሁሉ ሰማ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 የሰቂማም ሰዎች በተራሮች ራስ ላይ ድብቅ ጦር አደረጉ፤ መንገድ ተላላፊዎችንም ሁሉ ይዘርፉ ነበር፤ ለአቤሜሌክም ይህን አወሩለት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 የሴኬምም ሰዎች በተራሮች ራስ ላይ ድብቅ ጦር አደረጉ፥ መንገድ ተላላፊዎችንም ሁሉ ይዘርፉ ነበር፥ አቤሜሌክም ይህን ወሬ ሰማ። ምዕራፉን ተመልከት |