መሳፍንት 8:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ሌሎቹን ጌጣ ጌጦች ይኸውም የአንገት ሐብሉን ከነእንጥልጥሉ፥ የምድያም ነገሥታት ይለብሱት የነበረውን ሐምራዊ ልብስ ወይም በግመሎቻቸው አንገት ላይ ያሉትን ጌጦች ሳይጨምር ጌዴዎን በጠየቃቸው መሠረት የሰጡት የወርቅ ጉትቻ ክብደት ሺህ ሰባት መቶ ሰቅል ያህል መዘነ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ሌሎቹን ጌጣጌጦች፣ ይኸውም የዐንገት ሐብሉን ከነ እንጥልጥሉ፣ የምድያም ነገሥታት ይለብሱት የነበረውን ሐምራዊ ልብስ ወይም በግመሎቻቸው ዐንገት ላይ ያሉትን ጌጦች ሳይጨምር ጌዴዎን በጠየቃቸው መሠረት የሰጡት የወርቅ ጕትቻ ክብደት ሺሕ ሰባት መቶ ሰቅል ያህል መዘነ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 ጌዴዎን የተቀበለው የጆሮ ጒትቻ ኻያ ኪሎ ያኽል የሚመዝን ሆነ፤ ይህም ሌላውን ጌጣጌጥ፥ የአንገት ሐብልና የምድያማውያን ነገሥታት ይለብሱት የነበረውን ሐምራዊ ልብስ፥ እንዲሁም በግመሎቻቸው አንገት ዙሪያ ያለውን ጌጥ ሳይጨምር ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 የለመነውም የወርቅ ጕትቻ ሚዛኑ ከአምባሩ፥ ከድሪውም፥ የምድያምም ነገሥታት ከለበሱት ከቀዩ ቀሚስ፥ በግመሎቻቸውም አንገት ከነበሩት ሥሉሴዎች ሌላ ሺህ ሰባት መቶ ሰቅለ ወርቅ ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 የለመነውም የወርቅ ጉትቻ ሚዛኑ፥ ከአምባሩ፥ ከድሪውም፥ የምድያምም ነገሥታት ከለበሱት ከቀዩ ቀሚስ፥ በግመሎቻቸውም አንገት ከነበሩት ሥሉሴዎች ሌላ፥ ሺህ ሰባት መቶ ሰቅለ ወርቅ ነበረ። ምዕራፉን ተመልከት |