መሳፍንት 21:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ብንያማውያን እንደ ተባሉት አደረጉ፤ ልጃገረዶቹ በሚጨፍሩበትም ጊዜ እያንዳንዱ ሰው አንዳንድ እየጠለፈ ሚስት እንድትሆነው ይዞ ሄደ፤ ከዚያም ወደ ርስታቸው ተመለሱ፤ ከተሞቻቸውንም አድሰው በዚያ ኖሩ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ብንያማውያን እንደ ተባሉት አደረጉ፤ ልጃገረዶቹ በሚጨፍሩበትም ጊዜ እያንዳንዱ ሰው አንዳንድ እየጠለፈ ሚስት እንድትሆነው ይዞ ሄደ፤ ከዚያም ወደ ርስታቸው ተመለሱ፤ ከተሞቻቸውንም አድሰው በዚያ ኖሩ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ብንያማውያንም እንደዚሁ አደረጉ፤ በብዛታቸው ልክ እያንዳንዱ በሴሎ ከሚጨፍሩት ልጃገረዶች መካከል እየጠለፈ በሚስትነት ይዞ ሄደ፤ ወደ ግዛታቸውም ተመልሰው ከተሞቻቸውን በማደስ በዚያ ኖሩ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 የብንያምም ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ በቍጥራቸውም መጠን ከተነጠቁት ዘፋኞች ሚስትን ወሰዱ፤ ወደ ርስታቸውም ተመልሰው ሄዱ፤ ከተሞችንም ሠርተው ተቀመጡባቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 የብንያምም ልጆች እንዲሁ አደረጉ፥ በቁጥራቸውም መጠን ከተነጠቁት ዘፋኞች ሚስት ወሰዱ፥ ወደ ርስታቸውም ተመልሰው ሄዱ፥ ከተሞችንም ሠርተው ተቀመጡባቸው። ምዕራፉን ተመልከት |