መሳፍንት 21:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ስለዚህ በዚህን ጊዜ ብንያማውያን ተመለሱ፤ ከመገደል የተረፉትንም የኢያቢስ ገለዓድ ሴቶች ሰጧቸው፤ ይሁን እንጂ የሴቶቹ ቊጥር ለሁሉም የሚበቃ አልነበረም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ስለዚህ በዚህ ጊዜ ብንያማውያን ተመለሱ፤ ከመገደል የተረፉትንም የኢያቢስ ገለዓድ ሴቶች ሰጧቸው፤ ይሁን እንጂ የሴቶቹ ቍጥር ለሁሉም የሚበቃ አልነበረም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ብንያማውያንም ተመልሰው መጡ፤ ሌሎቹም እስራኤላውያን ከሞት በመትረፍ ከያቤሽ ተማርከው የመጡትን ልጃገረዶች ሰጡአቸው፤ ነገር ግን ቊጥራቸው ተመጣጣኝ ሆኖ አልተገኘም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 በዚያም ጊዜ የብንያም ልጆች ወደ እስራኤል ልጆች ተመለሱ፤ የእስራኤልም ልጆች ከኢያቢስ ገለዓድ ሴቶች ያዳኑአቸውን ሴቶች ሰጡአቸው። በዚህም ተስማሙ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 በዚያም ጊዜ የብንያም ልጆች ተመለሱ፥ ከኢያቢስ ገለዓድም ሴቶች ያዳኑአቸውን ሴቶች አገቡአቸው። ነገር ግን የሚበቁ ሴቶች አላገኙም። ምዕራፉን ተመልከት |