መሳፍንት 19:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ስለዚህ ሁለቱ ለመብላትና ለመጠጣት አብረው ተቀመጡ። የልጂቷም አባት፥ “እባክህ ዛሬም እዚሁ አድረህ ተደሰት” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ስለዚህ ሁለቱ ለመብላትና ለመጠጣት ዐብረው ተቀመጡ። የልጅቷም አባት፣ “እባክህ ዛሬም እዚሁ ዐድረህ ተደሰት” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ስለዚህ ሁለቱ ሰዎች ተቀምጠው አብረው ተመገቡ፤ የሴቲቱም አባት ሌዋዊውን “እባክህ ዛሬ ደስ ብሎህ እዚሁ ዕደር” አለው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ሁለቱም በአንድ ላይ ተቀመጡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ የብላቴናዪቱም አባት ሰውዬውን፥ “ዛሬ ደግሞ ከዚህ እደር ልብህንም ደስ ይበለው” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ተቀመጡም በአንድ ላይም በሉ ጠጡም፥ የብላቴናይቱም አባት ሰውዮውን፦ ዛሬ ደግሞ ከዚህ ለማደር፥ እባክህ፥ ፍቀድ፥ ልብህንም ደስ ይበለው አለው። ምዕራፉን ተመልከት |