Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መሳፍንት 18:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በሚካ ቤት አጠገብ እንደ ደረሱም የወጣቱን ሌዋዊ ድምፅ ዐወቁ፤ ስለዚህ ወደዚያ ጐራ ብለው፥ “ወደዚህ ያመጣህ ማን ነው? እዚህ ምን ትሠራለህ? የመጣኸውስ ለምንድን ነው?”። ሲሉ ጠየቁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በሚካ ቤት አጠገብ እንደ ደረሱም የወጣቱን ሌዋዊ ድምፅ ዐወቁ፤ ስለዚህ ወደዚያ ጐራ ብለው፣ “ወደዚህ ያመጣህ ማን ነው? እዚህ ምን ትሠራለህ? የመጣኸውስ ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እዚያም በነበሩበት ጊዜ ወጣቱን ሌዋዊ በአነጋገሩ ሁኔታ ከየት እንደ ሆነ ለይተው ዐወቁት፤ ወደ እርሱም ቀርበው “እዚህ ምን ትሠራለህ፤ ወደዚህ ያመጣህስ ማነው?” ሲሉ ጠየቁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በሚካ ቤትም በነ​በሩ ጊዜ የሌ​ዋ​ዊ​ዉን የጐ​ል​ማ​ሳ​ውን ድምፅ ዐወቁ፤ ወደ እር​ሱም ቀር​በው፥ “ወደ​ዚህ ማን አመ​ጣህ? በዚ​ህስ የም​ታ​ደ​ር​ገው ምን​ድን ነው? በዚ​ህስ ምን አለህ?” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በሚካ ቤት አጠገብም በነበሩ ጊዜ የሌዋዊውን የጕልማሳውን ድምፅ አወቁ፥ ወደ እርሱም ቀርበው፦ ወደዚህ ማን አመጣህ? በዚህስ የምታደርገው ምንድር ነው? በዚህስ ምን አለህ? አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መሳፍንት 18:3
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከጥቂት ጊዜ በኋላ በዚያ ቆመው የነበሩት ጠጋ ብለው ጴጥሮስን “በእውነት አንተም ከእነርሱ ወገን ነህ፤ አነጋገርህ ያስታውቅብሃልና” አሉት።


መቃብር በዚህ ያስወቀርህ፥ ከፍ ባለው ሥፍራ መቃብር ያሠራህ፥ በድንጋይም ውስጥ ለራስህ መኖሪያ ያሳነጽክ በዚህ ስፍራ ምን መብት አለህ? በዚህስ ለአንተ ወገን የሆነ ማን አለ?


እስቲ “ሺቦሌት” በል ይሉታል፤ ታዲያ ቃሉን በትክክል ማለት ሳይችል ቀርቶ “ሲቦሊት” ካለ ይዘው እዚያው መሻገርያው ላይ ይገድሉታል፤ በዚያ ጊዜም አርባ ሁለት ሺህ ኤፍሬማውያን ተገደሉ።


ያዕቆብም ወደ አባቱ ወደ ይስሕቅ ቀረበ፥ ዳሰሰውም፥ እንዲህም፦ “ይህ ድምፅ የያዕቆብ ድምፅ ነው፥ እጆቹ ግን የዔሳው እጆች ናቸው” አለው።


ስለዚህ ዳናውያን ምድሪቱን እንዲሰልሉና እንዲመረምሩ አምስት ኃያላን ሰዎች ከጾርዓና ከኤሽታኦል ከተሞች ወደዚያ ላኩ፤ እነዚህም ነገዶቻቸውን ሁሉ የሚወክሉ ነበሩ። የላኳቸውም ሰዎች፥ “ሂዱ፤ ምድሪቱን ሰልሉ” አሏቸው። መልእክተኞቹም ወደ ኰረብታማው የኤፍሬም አገር ገቡ፤ ወደሚያድሩበትም ወደ ሚካ ቤት መጡ።


እርሱም፥ “ሚካ ይህን ይህን አደረገልኝ፥ ቀጠረኝ፤ ካህኑም ሆንሁ” አላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች