መሳፍንት 17:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 አንድ ሺህ አንድ መቶውን ሰቅል ብር በመለሰላት ጊዜ፥ እናቱ “ብሬን የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት ለማበጀት ስለ ልጄን ለጌታ እቀድሰዋለሁ፤ አሁንም ለአንተው መልሼ እሰጥሃለሁ” አለችው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 አንድ ሺሕ አንድ መቶውን ሰቅል ብር በመለሰላት ጊዜ እናቱ፣ “ብሬን የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ጣዖት ለማበጀት ስለ ልጄ ለእግዚአብሔር እቀድሰዋለሁ፤ አሁንም ለአንተው መልሼ እሰጥሃለሁ” አለችው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ልጁም ገንዘቡን መልሶ ለእናቱ ሰጣት፤ እርስዋም “እኔ ራሴ ብሩን ለእግዚአብሔር ስለ ልጄ የተለየ አደርገዋለሁ፤ ከእንጨት ተሠርቶ በብር የተለበጠ ጣዖት ማሠሪያም ይሆናል፤ ስለዚህ ብሩን ለአንተ መልሼ እሰጥሃለሁ” አለችው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 አንዱን ሺህ አንድ መቶ ብርም ለእናቱ መለሰላት፤ እናቱም፥ “ይህን ብር የተቀረፀ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል አድርጌ ከእጄ ስለ ልጄ ለእግዚአብሔር እቀድሰዋለሁ፤ አሁንም ለአንተ እመልሰዋለሁ” አለች። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 አንዱን ሺህ እንዱን መቶ ብርም መለሰላት፥ እናቱም፦ ይህን ብር የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል አድርጌ ከእጄ ስለ ልጄ ለእግዚአብሔር እቀድሰዋለሁ፥ አሁንም ለአንተ እመልሰዋለሁ አለች። ምዕራፉን ተመልከት |