መሳፍንት 13:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ነገር ግን፥ ‘ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጪ፤ ርኩስ ነገር አትብይ፤ ልጁም ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ናዝራዊ በመሆን ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናልና’ ብሎኛል።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ነገር ግን፣ ‘ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጪ፤ ርኩስ ነገር አትብዪ፤ ልጁም ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ናዝራዊ በመሆን ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናልና’ ብሎኛል።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ነገር ግን እርሱ ‘እነሆ ትፀንሺአለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ’ ብሎ ነገረኝ፤ እንዲሁም የሚወለደው ልጅ ከተወለደበት ቀን ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ በናዝራዊነት ለእግዚአብሔር የተለየ ስለሚሆን፥ የወይን ጠጅም ሆነ ማንኛውንም የሚያሰክር መጠጥ ከመጠጣትና ማንኛውንም ርኩስ ምግብ ከመብላት እንድጠነቀቅ ነግሮኛል።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 እርሱም፦ እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ እንግዲህ የወይን ጠጅንና የሚያሰክር መጠጥን አትጠጪ፥ ርኩስ ነገርንም አትብዪ፤ ልጁ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና አለኝ” ብላ ተናገረች። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 እርሱም፦ እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፥ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና አሁን የወይን ጠጅ የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ አለኝ ብላ ተናገረች። ምዕራፉን ተመልከት |