መሳፍንት 10:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 የገለዓድ ሕዝብ አለቆችም እርስ በእርሳቸው፥ “በአሞናውያን ላይ ጦርነቱን የሚጀምር ሰው በገለዓድ ነዋሪዎች ሁሉ ላይ አለቃ ይሆናል” ተባባሉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 የገለዓድ ሕዝብ አለቆችም እርስ በርሳቸው፣ “በአሞናውያን ላይ ጦርነቱን የሚጀምር ሰው በገለዓድ ነዋሪዎች ሁሉ ላይ አለቃ ይሆናል” ተባባሉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 በዚያም ሕዝቡና በገለዓድ የእስራኤላውያን የነገድ አለቆች ሁሉ “ዐሞናውያንን ስንወጋ መሪ የሚሆነን ማነው? ጦርነቱን የሚከፍት ሰው እርሱ በገለዓድ ለሚኖር ሰው ሁሉ መሪ ይሆናል” ተባባሉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 የገለዓድ ሕዝብ አለቆችም እርስ በርሳቸው፥ “ከአሞን ልጆች ጋር መዋጋትን የሚጀምር ማን ነው? እርሱ በገለዓድ ሰዎች ሁሉ ላይ አለቃ ይሆናል” አሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ሕዝቡም፥ የገለዓድ አለቆች፥ እርስ በእርሳቸው፦ ከአሞን ልጆች ጋር መዋጋት የሚጀምር ማን ነው? እርሱ በገለዓድ ሰዎች ሁሉ ላይ አለቃ ይሆናል አሉ። ምዕራፉን ተመልከት |