Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ይሁዳ 1:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ይህም በሁሉ ላይ ለመፍረድ ነው፤ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኀጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዐመፀኞችም ኀጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኀጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ይህም፣ በሰው ሁሉ ላይ ለመፍረድ እንዲሁም ዐመፀኞችን ሁሉ በክፋት መንገድ በሠሩት የዐመፅ ሥራና በክፋት በርሱ ላይ ስለ ተናገሩት የስድብ ቃል ሁሉ አጥፊነታቸውን ይፋ ለማድረግ ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እነዚያን እግዚአብሔርን የማያመልኩትን ሰዎች ባደረጉአቸው ክፉ ነገሮች ምክንያት ይቀጣቸዋል፤ እግዚአብሔርም በእውነቱ በእነዚህ እርሱን በማያመልኩ ኃጢአተኞች ላይ በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩአቸው ክፉ ነገሮች ሁሉ ይፈርድባቸዋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ይሁዳ 1:15
35 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በክፋት ይናገሩብሃልና፥ ጠላቶችህም በከንቱ ያምፁብሃል።


የተጻፈውን ፍርድ ያደርጉባቸው ዘንድ። ለቅዱሳን ሁሉ ይህች ክብር ናት። ሃሌ ሉያ።


አቤቱ፥ አንተን ጠርቻለሁና አልፈር፥ ክፉዎች ይፈሩ በሲኦልም ዝም ይበሉ።


ጽድቅህን እንደ ብርሃን። ፍርድህንም እንደ ቀትር ያመጣዋል።


በሰማይ ላይ በድፍረት ተናገሩ፥ አንደበታቸውም በምድር ውስጥ ተመላለሰ።


ይደነፋሉ፥፥ ክፉ አድራጊዎች ይታበያሉ።


ዓለምንም በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።


ሙሴም፦ “ጌታ በማታ የምትበሉትን ሥጋና በማለዳ ደግሞ የሚያጠግባችሁን ምግብ ሲሰጣችሁ ጌታ ያጉረመረማችሁበትን ማጉረምረም ሰምቶ ነው፤ እኛ ምንድን ነን? ማጉረምረማችሁ በጌታ ላይ ነው እንጂ በእኛ ላይ አይደለም” አለ።


አንተ ጐበዝ፥ በጉብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጉብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፥ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ እወቅ።


እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።


በአፋችሁ ታበያችሁብኝ፥ ንግግራችሁንም በእኔ ላይ አበዛችሁ፤ እኔም ሰምቼዋለሁ።


የሰው ልጅም ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው።


ቀንቀጥሮአልና፤ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።”


አንተም በወንድምህ ላይ ስለምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለምን ትንቃለህ? ሁላችን በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና።


ይህም እኔ በወንጌል እንዳስተማርሁት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር የሰዎችን የተሰወሩ ነገሮች በሚፈርድበት ቀን ይሆናል።


ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሓ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቁጣ ቀን በራስህ ላይ ቁጣን ታከማቻለህ።


ስለዚህም፥ በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን የሚያወጣ ደግሞም የልብን ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ፥ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም እያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።


በውጭ ባሉት ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት።


ይህንንም በመረዳት ሕግ የተሠራው ለጻድቃን ሳይሆን ይልቁንስ ለበደለኞችና ለማይታዘዙ፥ ለዐመጸኞችና ለኀጢአተኞች፥ ቅድስና ለሌላቸውና ለርኩሳን፥ አባትና እናትን ለሚገድሉ፥ ለነፍሰ ገዳዮች፥


እነዚህ የሚያጉረመርሙ፥ የሚያማርሩ፥ ክፉ ምኞታቸውን የሚከተሉ ናቸው፤ አፋቸው የትዕቢት ቃልን ይናገራል፤ለጥቅማቸው ሲሉ ሰዎችን ያደንቃሉ።


ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፤ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር።


ይህን የሚመሰክር “አዎን በቶሎ እመጣለሁ፤” ይላል። አሜን፤ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።


እጅግ በመኩራራት አትናገሩ፥ የእብሪትም ቃል ከአፋችሁ አይውጣ፥ ጌታ አምላክ አዋቂ ነውና፥ በእርሱም ሥራዎች ይመዘናሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች