Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 9:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 አለቆቹም ሁሉ ለማኅበሩ ሁሉ እንዲህ አሉአቸው፦ “በእስራኤል አምላክ በጌታ ምለንላቸዋል፤ ስለዚህም እንነካቸው ዘንድ አይገባንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ነገር ግን መሪዎቹ ሁሉ ለማኅበሩ እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ስለማልንላቸው፣ አሁን ጕዳት ልናደርስባቸው አንችልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 መሪዎቹ ግን እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ቃል ገብተንላቸዋል፤ ስለዚህም አሁን ጒዳት ልናደርስባቸው አይገባም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 አለ​ቆ​ቹም ሁሉ ለማ​ኅ​በሩ ሁሉ፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምለ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ ስለ​ዚ​ህም እን​ነ​ካ​ቸው ዘንድ ምንም አን​ች​ልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 አለቆቹም ሁሉ ለማኅበሩ ሁሉ፦ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ምለንላቸዋል፥ ስለዚህም እንነካቸው ዘንድ አይገባንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 9:19
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔ፦ በመለኮታዊ መሐላ መሠረት የንጉሥን ትእዛዝ ጠብቅ እልሃለሁ።


የጻድቁና የበደለኛው፥ የመልካሙና የክፉው፥ የንጹሑና የርኩሱ፥ መሥዋዕትን የሚሠዋውና የማይሠዋው፥ የሰው ሁሉ ድርሻው አንድ ነው፤ መልካሙ ሰው እንደ ኃጢአተኛው፥ የሚምለው ሰው መሐላን እንደሚፈራው ነው።


‘በሕያው ጌታ እምላለሁ!’ ብለህም በእውነትና በቅንነት በጽድቅም ብትምል፥ አሕዛብ እራሳቸውን በእርሱ ይባርካሉ በእርሱም ይመካሉ።”


የሕዝቡም አለቆች በእስራኤል አምላክ በጌታ ስለ ማሉላቸው የእስራኤል ልጆች አልመቱአቸውም። ማኅበሩም ሁሉ በአለቆቹ ላይ አጉረመረሙ።


ስለ ማልንላቸው መሓላ ቁጣ እንዳይወርድብን ይህን እናድርግባቸው፥ በሕይወትም እንዲኖሩ እንተዋቸው።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች