Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 8:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ኢያሱም ሰደዳቸው፤ ወደሚደበቁበትም ስፍራ ሄዱ፥ በጋይና በቤቴል መካከልም በጋይ በምዕራብ በኩል ተቀመጡ፤ ኢያሱ ግን በዚያች ሌሊት በሕዝቡ መካከል አደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም ኢያሱ ሰዎቹን ላካቸው፤ እነርሱም ሄደው ከጋይ በስተምዕራብ በቤቴልና በጋይ መካከል ባለው ቦታ አደፈጡ፤ ኢያሱ ግን እዚያው ከሕዝቡ ጋራ ዐደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከዚህ በኋላ ኢያሱ ወታደሮቹን ላከ፤ ከዐይ በስተምዕራብ በኩል በዐይና በቤትኤል መካከል ድብቅ ጦር ሆነው ቈዩ፤ ኢያሱም በሠራዊቱ መካከል ዐደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ኢያ​ሱም ላካ​ቸው፤ ወደ​ሚ​ደ​በ​ቁ​በ​ትም ስፍራ ሄዱ፤ በጋ​ይና በቤ​ቴል መካ​ከ​ልም በጋይ በባ​ሕር በኩል ተቀ​መጡ፤ ኢያሱ ግን በዚ​ያች ሌሊት በሕ​ዝቡ መካ​ከል አደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ኢያሱም ሰደዳቸው፥ ወደሚደበቁበትም ስፍራ ሄዱ፥ በጋይና በቤቴል መካከልም በጋይ በምዕራብ በኩል ተቀመጡ፥ ኢያሱ ግን በዚያች ሌሊት በሕዝቡ መካከል አደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 8:9
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የቤቴኤልና የዓይ ሰዎች፥ መቶ ሃያ ሦስት።


የቤት-ኤልና የዐይ ሰዎች፥ ሁለት መቶ ሀያ ሦስት።


አምስት ሺህ ያህል ሰዎችንም ወስዶ በቤቴልና በጋይ መካከል በከተማይቱም በምዕራብ በኩል ደብቆ አስቀመጣቸው።


ኢያሱም ከቤቴል በምሥራቅ በኩል በቤትአዌን አጠገብ ወዳለችው ወደ ጋይ ሰዎችን ከኢያሪኮ ላከ፤ እንዲህም አላቸው፦ “ውጡ ምድሪቱንም ሰልሉ፤” ሰዎቹም ወጡ፥ ጋይንም ሰለሉ።


ስለዚህ እጅ መንሻው ከእርሱ ቀድሞ አለፈ፥ እርሱ ግን በዚያች ሌሊት እዚያው በሰፈሩበት አደረ።


ከዚያም በቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራ ወጣ፥ በዚያም ቤቴልን ወደ ምዕራብ ጋይን ወደ ምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፥ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ።


በያዛችኋትም ጊዜ ከተማይቱን በእሳት አቃጥሉአት፤ እንደ ጌታ ቃል አድርጉ፤ እነሆ፥ አዝዣችኋለሁ።”


ኢያሱም ማልዶ በጠዋት ተነሣ፥ ሕዝቡንም ሰበሰበ፤ እርሱም ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋር ከሕዝቡ በፊት ወደ ጋይ ወጡ።


ይህንም፥ በቤትኤል፥ በደቡብ ራሞትና በያቲር ለነበሩ ላከላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች