ኢያሱ 8:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 የጋይንም ንጉሥ እስከ ማታ ድረስ በዛፍ ላይ ሰቀለው፤ ፀሐይም በገባች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፥ ሬሳውንም ከዛፍ አወረዱት፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ጣሉት፥ በእርሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 የጋይንም ንጉሥ በዛፍ ላይ ሰቀለው፤ ሬሳውንም እስኪመሽ ድረስ እዚያው እንዳለ ተወው፤ ፀሓይ ስትጠልቅም፣ ኢያሱ ሬሳውን እንዲያወርዱትና በከተማው በር ላይ እንዲጥሉት አዘዘ፤ የትልልቅ ድንጋይ ቍልልም ከመሩበት፤ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ እዚያው ይገኛል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 የዐይንም ከተማ ንጉሥ በእንጨት ላይ ሰቅሎ ሬሳው እስከ ማታ ተንጠልጥሎ እንዲቈይ አደረገ። ፀሐይም በምትጠልቅበት ጊዜ ሬሳው ከተሰቀለበት እንጨት ላይ ወርዶ በከተማይቱ ቅጽር በር መግቢያ እንዲጣል አደረገ፤ በእርሱም ላይ ብዙ የድንጋይ ቊልል ከመሩበት፤ የድንጋዩም ቊልል እስከ አሁን በዚያው ይገኛል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 የጋይንም ንጉሥ በዝግባ ዛፍ ላይ ሰቀለው፤ እስከ ማታም ድረስ በዛፉ ላይ ቈየ። ፀሐይም በገባች ጊዜ ኢያሱ ያወርዱት ዘንድ አዘዘ፤ ከዛፉም አወረዱት፤ በከተማዪቱም በር አደባባይ ጣሉት፤ በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 የጋይንም ንጉሥ እስከ ማታ ድረስ በዛፍ ላይ ሰቀለው፥ ፀሐይም በገባች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፥ ሬሳውንም ከዛፍ አወረዱት፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ጣሉት፥ በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት። ምዕራፉን ተመልከት |