Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 23:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “እነሆም፥ ዛሬ የምድርን ሁሉ መንገድ እሄዳለሁ፤ እናንተም ጌታ ስለ እናንተ ከተናገረው ከመልካም ነገር ሁሉ አንድ ነገር እንዳልቀረ በልባችሁ ሁሉ በነፍሳችሁም ሁሉ እወቁ፤ ሁሉም ነገር ተከነናውኖላችኋል፤ ከእርሱም አንድም የቀረ ነገር የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “እነሆ፤ አሁን የምድርን ሁሉ መንገድ ልሄድ ነው፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ መልካም ተስፋ ሁሉ አንዲቱን እንኳ እንዳላስቀረባችሁ፣ በፍጹም ልባችሁ በፍጹም ነፍሳችሁ ታውቃላችሁ፤ አንዱም ሳይቀር ሁሉም ተፈጽሟል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “እነሆ እኔ የምሞትበት ጊዜ ደርሶአል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ያደረገላችሁን መልካም ነገር ሁሉ ከእናንተ እያንዳንዱ በፍጹም ልቡና በፍጹም ነፍሱ ያውቃል፤ እርሱ ከሰጣችሁ ተስፋ አንድም ሳይቀር ሁሉም ተፈጽሞአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “እኔም በም​ድር እን​ዳ​ሉት ሰዎች ሁሉ ዛሬ ወደ መን​ገድ እሄ​ዳ​ለሁ፤ እና​ን​ተም አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኛ ከተ​ና​ገ​ረው ከመ​ል​ካም ነገር ሁሉ አንድ ነገር እን​ዳ​ል​ቀረ በል​ባ​ችሁ ሁሉ፥ በነ​ፍ​ሳ​ች​ሁም ሁሉ ዕወቁ፤ ሁሉ ደር​ሶ​ናል፤ ከእ​ር​ሱም ያላ​ገ​ኘ​ነው የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እነሆም፥ ዛሬ የምድርን ሁሉ መንገድ እሄዳለሁ፥ እናንተም እግዚአብሔር ስለ እናንተ ከተናገረው ከመልካም ነገር ሁሉ አንድ ነገር እንዳልቀረ በልባችሁ ሁሉ በነፍሳችሁም ሁሉ እወቁ፥ ሁሉ ደርሶላችኋል፥ ከእርሱም አንድ ነገር አልቀረም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 23:14
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም።


“እነሆ እኔ ሰው ሁሉ እንደሚሞት የምሞትበት ጊዜ ተቃርቧል፤ እንግዲህ በርታ! ቆራጥ ሰው ሁን፤


አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ።


ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?


“በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ለሕዝቡ ሰላምን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ከሰጠውም መልካም ተስፋ ምንም የቀረ የለም።


ሳሙኤል አደገ፤ ጌታም ከእርሱ ጋር ነበረና፥ ከሚናገረው ቃል አንዳች በምድር አይወድቅም ነበር።


ከፍ ያለውን ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፥ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፈቃድም ሲጠፋ፥ ሰው ወደ ዘለዓለም ቤት ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፥


ከግብፃውያን እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወደ መልካምና ሰፊ አገር፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ከነዓናውያን፥ ሒቲያውያን፥ ኤሞራውያን፥ ፌርዛውያን፥ ሒዊያውያን፥ የቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።


ለሰዎችም አንድ ጊዜ ለመሞት ከዚያም ለፍርድ መቅረብ ተመድቦባቸዋል።


ለሞት፥ ሕያዋንም ሁሉ ለሚሰበሰቡበት ቤት አሳልፈህ እንደምትሰጠኝ አውቄአለሁና።”


እሰጣቸውም ዘንድ ወደ ማልሁላቸው ምድር ባገባኋቸው ጊዜ፥ ከፍ ያለውን ኮረብታ ሁሉ ቅጠልማውንም ዛፍ ሁሉ አዩ፥ በዚያም መሥዋዕታቸውን ሠዉ በዚያም የሚያስቆጣኝን ቁርባናቸውን አቀረቡ በዚያም ደግሞ ጣፋጩን ሽታቸውን አደረጉ በዚያም የመጠጥ ቁርባናቸውን አፈሰሱ።


የእስራኤልም የሞቱ ቀን ቀረበ፥ ልጁን ዮሴፍንም ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደሆንሁ እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ፥ በግብጽ ምድርም እንዳትቀብረኝ በታማኝነትና እውነት ቃል ግባልኝ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች